Monday, April 20, 2015

ሸክማችሁ የከበደ ደካሞች ሁሉ ወደ እኔ ኑ፡፡ ማቴ.፲፩÷፳፰ ክፍል ሶስት

ውድ አንባቢያን ሸክማችሁ የከበደ ደካሞች ሁሉ ወደ እኔ ኑ በሚል ርእስ በሁለት ተከታታይ ክፍል ያቀረብኩላችሁን ስብከት የመጨረሻውን ሶስተኛ ክፍል እነሆ፡፡ መልካም ንባብ::
ስለዚህ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፃማ ሓጢአት የደከማችሁ፣ፃዕረ ሞት የከበዳችሁ፤ያስመረራችሁ የሰው ልጆች ሁሉ በሕግ፣በአምልኮ፣በምግባር፣በንስሓ ወደ እኔ ኑ፣ቅረቡ እኔም በፍቅሬ አሳርፋችኋለሁ፣ሸክማችሁንም አቀልላችኋለሁ፡፡ወንጌል፣መስቀለ ሰላም፣ፍቅር ቀንበሬን ተሸከሙ እረፍተ ሥጋ እረፍተ ነፍስ ታገኛለችሁ፡

Wednesday, April 15, 2015

የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ



ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘየዓትት ኃጢአተ ዓለም የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ እንሆ”         ዮሐ. 1 29 የተወዳዳችሁ የዚህ ዓምድ አንባብያን የእግዚአብሔር ቸርነት የመላዕክት ተራዳኢነት የቅዱሳን አማላጅነት አይለያችሁ እያልኩኝ እነሆ ደግሞ ለዚህ ሳምንት የምትሆን ነዋ በግዑ የምትል አጭር ፅሑፍ ይዤላችሁ በየፌስ ቡካችሁ ብቅ ብያለሁ መልካም ንባብ ፡፡ ሁላችንም እንደምናውቀው በግ በጣም ተወዳጅ ገራም የጌታውን ድምፅ በሚገባ ጠንቅቆ የሚያውቅ ፣ ለማዳ የቤት እንሰሳ ነው ፡፡ ዮሐ. 10  14-15 ፡፡ ተንኮል የቤለበት የዋህ ሰው ስታዩ በግ ነው ! ትሱ የለም ? ዮናታን የተባለ አንድ ነቢይ ዳዊት በስውር የፈፀመውን በደለ በሰምና ወርቅ ሲያስረደው የለማዳ በግ ምሳሌ ነበር የተጠቀመው እንዲህ በማለትበአንድ ከተማ አንድ ባለጠጋ አንዱም ደኃ የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩ ፡፡

Thursday, April 9, 2015

ሕማማተ ክርስቶስ

ይትባረክ እግዚአብሔር ዘሰመየ ሕማማተ ወልዱ ክብረ ወስብሓተ

Thursday, April 2, 2015

፰. ሆሣዕና



ሆሣዕና ማለት መድኃኒት ማለት ነው ፡፡ ዕለቱ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ሆኖ ሆሣዕና በአርያም እየተባለ በምስጋና በይባቤ ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ የገባበት እለት ነው ፡፡
ቤዛ ዓለም ክርስቶስ በማዕከለ ምድር በቀራኒዮ አደባባይ ተሰቅሎ የአዳምን በደል በመደምሰስ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለህ  ብሎ የገባለትን ቃል ኪዳን ይፈጽምለት ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ ፡፡

Sunday, March 29, 2015

ሸክማችሁ የከበደ ደካሞች ሁሉ ወደ እኔ ኑ፡፡ ማቴ.፲፩÷፳፰


                        ክፍል ሁለት
ከዚህ ሁሉ ባሻገር እሰድራኤላውያኑ ሌሎች ብዙ ማህበራዊና መንፈሳዊ የሆኑ ከባድ ሸክሞች ነበሩባቸው፡፡የሮማውያንን የቅኝ ግዛት ቀንበር አሽቀንጥረው ለመጣል የተደራጁ አደጋ ጣይ ብዙ የነፃ አውጪ ግንባሮች፤በአንጻሩ ደግሞ እንደ ፈሪሳውያን፣ሰዱቃውያን፣ኤሴውያን የመሳሰሉ ሃይማኖታዊ ካባ ለባሽ ቡድኖች ነበሩ፡፡

Friday, March 27, 2015

ብርሃናዊ መልአክ

፯. ኒቆዲሞስ



ሰባተኛው እሑድ ኒቆዲሞስ ይባላል፡፡ በሌሊት ወደ ጌታ መጥቶ ይማር የነበረው የኒቆዲሞስን ታሪክ የሚያወሳ ስብከት ይሰበካል፤ መዝሙር ይዘመራል፡፡
ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊና የአይሁድ አለቃ ነው፡፡ ፈርሳውያን የጌታ ተቀዋሚዎች ናቸው፡፡ ኒቆዲሞስ በዘመኑ ከነበሩት ተላላቅ የአይሁድ ምሑራን አንዱ ነበር፡፡ ኒቆዲሞስ የሕግ አዋቂ፤ የሕግ ምሑር ነው፡፡

Monday, March 23, 2015

ሸክማችሁ የከበደ ደካሞች ሁሉ ወደ እኔ ኑ፡፡ ማቴ.፲፩÷፳፰

ክፍል አንድ
የትምህርቱ ዓላማ ፡-ድካማችንን ተገንዝበን ከድካማችን ሁሉ ወደሚያሰርፈን አምላክ እንድንቀርብ የንስሓ ጥሪን ማስተጋባት ነው፡፡
ሸክም የሚከብድ፣የሚያደክም፣የሚያሳስብ ከባድ ነገር ሲሆን፤የሸክም ምሥጢራዊ ትርጉሙ ደገሞ ሓጢአት፣መከራ፣በሽታ፣ችግር፣አደራ፣ሀላፊነትየመሳሰሉትን ያመለክታል፡፡በዚህ ትምህርታችን የምንማረው ስለአንድ ከባድ ቁስ ሳይሆን በዚህ በሸክም ምሥጢራዊ ትርጉም ላይ ተመርኩዘን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረውን ትምህርት በአጭሩ እንመለከታለን፡፡