Thursday, February 4, 2016

በአበው ብሂል እንጨዋወት

ረዥም አይደል አጭር፣
ወፍራምም አይደል ቀጭን፣
ታግሎ የጣለኝ ከሰው ደጅ፣
እኔን ያኸል ነው እንጂ፡፡

ጥያቄ፡ ሀ. ሕብረ ቃሉ .......................................................... ነው፡፡
        ለ. ሰሙ …………………………………………………………………. ነው፡፡
        ሐ. ወርቁ ………………………………………………………………. ነው፡፡

ከመላእክት ጋር አንድ አድርገን

አቤቱ የእያንዳንዱን ልመናውን አሰብ፤ አቤቱ እያንዳንዱን ከእናቱ ማኅፀን ጀምረህ አስብ፤ በቀናች ሃይማኖት የሚኖሩትን ብዙ አሕዛብ አስብ፤ ሴቶቻቸውን ጠብቅ፤ ጎልማሶቻቸውን አቅና፤ ሽማግሎቻቸውን አጽና፤