Wednesday, April 15, 2015

የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ



ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘየዓትት ኃጢአተ ዓለም የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ እንሆ”         ዮሐ. 1 29 የተወዳዳችሁ የዚህ ዓምድ አንባብያን የእግዚአብሔር ቸርነት የመላዕክት ተራዳኢነት የቅዱሳን አማላጅነት አይለያችሁ እያልኩኝ እነሆ ደግሞ ለዚህ ሳምንት የምትሆን ነዋ በግዑ የምትል አጭር ፅሑፍ ይዤላችሁ በየፌስ ቡካችሁ ብቅ ብያለሁ መልካም ንባብ ፡፡ ሁላችንም እንደምናውቀው በግ በጣም ተወዳጅ ገራም የጌታውን ድምፅ በሚገባ ጠንቅቆ የሚያውቅ ፣ ለማዳ የቤት እንሰሳ ነው ፡፡ ዮሐ. 10  14-15 ፡፡ ተንኮል የቤለበት የዋህ ሰው ስታዩ በግ ነው ! ትሱ የለም ? ዮናታን የተባለ አንድ ነቢይ ዳዊት በስውር የፈፀመውን በደለ በሰምና ወርቅ ሲያስረደው የለማዳ በግ ምሳሌ ነበር የተጠቀመው እንዲህ በማለትበአንድ ከተማ አንድ ባለጠጋ አንዱም ደኃ የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩ ፡፡
ባለጠጋው እጅግ ብዙ በግና ላም ነበረው ፡፡ ለድኃው ግን ከገዛች አንዲት ታናሽ በግ በቀር አንዳች አልነበረውምብሎ የበግን ለማዳነት ሲገልፅ ሲዘርዝርአሳደጋትም ከልጆቹም ጋር በእርሱ ዘንድ አደገች እንጀራውንም ትበላ ፣  ከዋንጭውንም ትጠጣ ፣ በብቱም ትተኛ ነበር አንደ ልጁም ነበረች ይላል ፡፡ 2ሳሙ. 12 1-3
በግ ስጋው
ü  ለምግብነት ዘዳ. 14  4
ü  ለመሰዋዕትነት. ዘፍ 4 2 ዘሌ. 221 9
ü  እንዲሁም ፀጉሩ ተሸልቶ ዘፍ. 38 12
ü  ቆዳውም ተልጦ ለልብስነትና ለምንጣፍ ጥቅም ይውላል ዕብ. 11 37
ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኔታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዋሁን መስለው ከሚያስተምሩ ሐሰተኞች ነቢያትና አስተማሪዎች አስተምህሮ እንድንጠበቅ ስያስጠነቅቀንየበግ ለምድ ለብሰው እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁማቴ. 7 15 ብሏል ፡፡ ውድ አንባያን እስቲ ለአንድ አፍታ ቆሞ በሉና በጥሙና ሆናችሁ አስላስሉት በመካከላችሁ በምትማሩበት ሰንበት ትምህርት ቤት ፣ በምታስቀድሱበት ቤተክርስቲያን የጠመጠሙ የቆብ ጭምብል ያጣለቁ ውስጣቸው ዓውደ ነገሦት ላይ ላያቸው መቁጠሪያና ሰንሰለት የታጠቁ፣ ኧረ ከዝያም አልፎ በቅስናም ሆነ በመዘምርነት ተቀጥረው በነ ስም አይጠሩ ሳምባ የሚተነፍሱ አፃራረ ቅዱሳን ግዕዝ ጠቃሾች ከቅዳሴ መልስ ባዕድ ልሳን አነብናቢዎች አይታችሁ አታውቁምን? በእውነት ካላያችሁ ብፁዓን ናችሁ ፡፡ ይቅርታ ወደ አንዱ አዳራሽ ሳልገባ ወደ ርእሴ ልመለስ ፡፡
 ከተስፋይቱ ምድር ከምድረ ከነአን በጠፋ ጊዜ ዘፍ. (47 13) የያዕቆብ ልጆች የሚላስ የሚቀመስ አጥተው ሰባ 70 ነፍስ ሆነው ወደ ግብፅ ወርደዋል ዘፍ 46 25 ከነአን ማለት እግዚአብሔር በዝያ አለ ማለት ሲሆን ማርና ወተት በብዛት የሚመረትባት ለም አገር የበረከት ተምሳሌት ናት ፡፡ ግብፅ ዳግሞ የገሃነም የሲኦል ምሳሌ ነች ፡፡ እነዚህ የያዕቆብ ልጆች እግዚአብሔር ካለበት ስፍራ ተነቅለው በወቅቱ አረማውያን ወደ ነበሩበት አገር መሰደዳቸው እግዚኦ ሊያሰኝችሁ ይችላል፡፡ ግን እኮ እናንተም ጣታችሁ ወደ እነሱ ትቀስራላችሁ እንጂ እሁድ ከቅዳሴ መልስ አዋቂ ቤት ወይም ፓስተር ቤት ትገኙ ይሆናል! ማን ያውቃል? የያዕቆብ ልጆተ በዝያ ግዚአብሔ በበረከት በረድኤት በሌለበት ሲኦላዊት ግብፅ ለአራት መቶ ሰላሳ ዓመታት ምፃተኞችና ባሪያዎች ሆነው ከኖሩ በኋላ (የሓዋ. 7 6) 600000 ሰው በላይ ሆነው በነፃነት ለመኖር እጅግ በፀናችና በጠነከረች የእግዚአብሔር ክንድ ሲወጡ ነውር የሌለበት በግዓ ፋሲካን አርደው ደሙን በመርጨት ቀሳፊ መልአክ ሞተ በኩር መቅሰፍት ድነዋል ፡፡ ዘፀ. 12 ሙሉውን ምዕራፍ በማስተዋል ካነበብን ፋሲካ እንዴት እንደሆነና አምላካዊ ዓላማው በሚገባ እናውቃለን ፡፡ የፋሲካ በግ ከዚሁ ከግብፅ ከወጡበት ማግስት ጀምሮ እስከ ዘመነ ክርስቶስ 1500 ዓመታት ያህል ለእግዚአብሔር ተወዳጅ መስዋዕት እየሆነ መጥቷል ፡፡
ü  ለሚቃጠል መስዋዕት ዘሌ. 1 10
ü  ለድህንነት መስዋዕት ዘሌ 3 6
ü  ለኃጢአት መስዋዕት ዘሌ 43 2
ü  ለበደል መስዋዕት ዘሌ 51 5
እየቀረበ ስጋው እየተወራረደ ደሙ እየተረጨ ቆይቷል፡፡ ይህ ሁሉ መስዋዕት ለኃጢአታችን ስርየት ለበደላችን ካሳ ለድህነታችን ዋስትና ለመሆን ለሶስት የጨለማ ሰዓታት ያህል በመስቀል ላይ ፀዋትወ መከራ የተቀበለ አማናዊ መስዕት ሰማያዊ በግ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ያመለከት ነበር ፡፡ እነዚህ በየቀኑ ሲሰዉ የነበሩት የብሉይ ኪዳን መስዋስቶች በአዳምና በሔዋን አማካኝነት ወደ ዓለም የገባ ኃጢአት (ጥንተ አብሶ) ሮሜ. 5 12 ካስከተለው ፍደ ሰውን መታደግ አልቻሉም ነበር ፡፡ ይልቁንም እንደ ጥላ እንደ መርግፍ ሆነው የሚመጣውነዋ በግዑተብሎ የተመሰከረለት ጌታችንን እንደ መስተዋት ቁልጭ አድርገው ያሳያሉ እንጂ ፣ ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራውያን 4 9 -10 እንዲ ሲል ፅፏል “… መባና መስዋዕት ያቀርባሉ እነዚህ እስከ መታደስ ዘመን ድረስ የተደረጉ ስለ ምግብና ስለ መጠጥም ስለ ልዩ ልዩ መታጠብ የሚሆኑ የስጋ ስረዓቶች ብቻ ናቸውና የሚያመልከውን በህሊና ንፁህ ልያደርጉት አይችሉም ፡፡ እነዚ ሁሉ ሰውን አንፅተው ወደ እግዚአብሐር ማቅረብ አልቻሉም ነበር :: የአማናዊው በግ ደም ግን ከንዑሳትና ከዓበይት ኃጣውዕ ከእኩያት ፍትወታታ ያነፃል ፡፡ወደሙ ለኢየሱስ ክርስቶስ ያነፃሐነ እምኩሉ ኃጣውኢነእንጂ ይላል፡፡ የብሉይ ኪዳን የመስዋት ህግ የሚያበቃበት ዘመን ሲፈፀም እግዚአብሔር ከዓመታት አንድ ዓመት ከወራት አንድ ወር ከሳምንታት አንድን ሳምንት ከሰዓታት አንድ ደቂቃ ሳያጎድል ልጁን ለሕማም ለሞት በመስዋት አሳልፎ ሰጠ :: ገላ. 4 4
ዛሬ ፋሲካ (ስቅለት) እያልን የምናከብረው ቀን ከዛሬ ሁለተ ሺ ዓመት በፊት ነውርና እንከን የሌለበት ንፁሐ ባሕርይ የአዲስ ኪዳን አማናዊ በግ ክርስቶስ በቀራንዮ ዕፀ መስቀል ላይ የተሰዋበት ቀን ነው ፡፡ ጥዑመ ልሳን ሐዋርይው 1ቆሮ. 5 7 “አሮጌውን እርሾ አስወግዱ ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶልናብሏል ይህ አባባል ብሉይ ኪዳን ስፍራውን ለአዲስ ኪዳን እንደለቀቀ ያሰረዳናል ፡፡ ዕብ. 8 13
 ጌታችን ሲሰዋ የብሉይ ኪዳን መስዋዕቶች አገልግሎቸው ተፈፅሟል ፡፡ የመጣው ህግና ነቢያትን ለመፈፀም ስለሆነ ማቴ. 5 7 :: ምናልባት እስከ አሁን በብሉይ የመስዋዕት ህግ ተጋርዳችሁ ከሆነ ወደ መስቀሉ ትኩር ብላችሁ የሃይማኖታችን ሐዋሪያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ትመለከቱን ዘንድ ዕብ. 3 1 የዘወትር ፀሎታችን ነው ፡፡ መስዋዕቱ ፍፃሜ ያገኘው ጌታችን በትክክለኛ ጊዜ በፋሲካ በዓል በፈፀመው የስርዓት መስዋዕትነው፣ ይህም በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የነበረ ግንኙነት አዲስ መልክ አስይዟል ፡፡ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል :: ዓመት ፍዳ ዓመት ኩነኔ በዓመተ ምህረት በዓመተ እድገት ቀይሯል ፡፡ በመስቀል ላይ በፈሰሰ ደሙ አማካኝነት አዲሱን ኪዳን መስርቷል ፡፡ስለ ብዙዎት ለኃጢአት ይቅርተ የሚፈሰው ደሜ ይህ ነውማቴ. 26 28 ይላል የአዲሱ ኪዳን መስዋዕትነውር የሌለበት ሆኖ ለዘለዓለም መንፈስ ራሱ ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔር ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ህሊናችሁ ይነፃ ይሆን ዕብ. 9 14 ተብሎ ተመስክሮለታል ፡፡
ውድ አንባብን የክርስቶስ ደም እምነት ከሌው ከሙት ስራ ህሊናን ያነፃል ያጠራል ይቀድሳል :: በዚሁ በፈሰሰ ደም የሐጢአት ስርየት ተከናውኗል :: ሮሜ. 3 25 በመስቀል መሰውያ የተሰዋው አማናዊው በግ ክርስቶስራሱን የመዓዛ ሽታ የሚሆን መባና መስዋዕት አድጎ አቅርቧል :: አፌ.5 2 እግዚአብሔርን ያስገረመ መስዋዕት ነውወአንከሩ አብ እምዝንቱ መስዋዕት ይለዋል :: ስለዚህ አኛንም ራሳችንን ቅዱስና ህያው መስዋዕት አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርህራሄ እለምናችኋላሁ ሮሜ. 12 1 እያለ ሐዋርያው የሳስበናል :: የእስራኤል ልጆች ከእግዚአብሔር ቁጣ የዳኑት በበጉ ደም ነው :: የደሙ ምልክት በሌላቸው ስዎች ላይ የእግዚአብሔ ቁጣ ተገልጧል :: ዛሬ በቀራንዮ የተስዋው የእግዚአብሔር በግ ከእግዚኣብሔር ቁጣ የዳንበት ከእግዚኣብሔር ጋር የታረቅንበት መርገመ ስጋ መርገመ ነፍስ የጠፋበት አዳምና ልጆች የተዋጁበት ዲያብሎስ የተሻረበት መስዋት ነው ፡፡ ይቆየን ይቀጥላል…፡፡


ከመምህር ጽጌ

No comments:

Post a Comment