Wednesday, April 27, 2016

አይቴ ሀሎ በግዑ ለመሥዋዕት? ዘፍ. ፳፪፥፯

            በዲ/ን ዓለማየሁ ሀብቴ
              ክፍል ፪  
በሓዲስ ኪዳን የዓለምን ኃጢአት አስወግዶ ሰውን ከአምላኩ ያስታረቀው የተወደደው የመስዋዕቱ በግ ነው፡፡ ይህ የመሥዋዕቱ በግ ለዘመናት ሲጠየቅ የኖረው የእግዚአብሔር በግ ነው፡፡ የመሥዋዕቱ በግ የት አለ? ብሎ ይስሐቅ ለጠየቀው ጥያቄ ትክክለኛው መልስ የተገኘው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአጭር ቁመት፣ በጠባብ ደረት ተወስኖ፣ በኩነተ ሰብእ፣ በለቢሰ ሥጋ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደ ጊዜ ነው፡፡ የመሥዋዕቱም በግ መገኘቱን ለይስሐቅ (ለዓለም) የነገሩት መጋቤ ሓዲስ፣ አብሳሬ ትስብእት፣ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤልና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሓንስ ናቸው፡፡