አስተበቊዓክሙ ከመ ትትወከፍዋ ለሃይማኖት እንተ ተውህበት ሎሙ ለቅዱሳን፡፡ ይሁ. 1፥ 3
በመምህር ጽጌ
ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈፅሞ ስለ ተገለጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ:: የሃይማኖት ስር መሠረቱ በሰብአዊ ፍጡር ምርመር የተገኘ፣ በስነ መለኮት ምሁራን አስተያየት ተሰጥቶበት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ፣ እየተመረመረ ሲወርዱ ሲዋረደ እኛ ዘንድ የደረሰ የእምነት ዕቃ አይደለም፡፡ ወይም ጥላ እሸት ቀቢዎች እንደሚያሰራጩት ውስጡን ሳናውቀው ከውጪ አገር በአደራ የመጣልን የታሸገ ፓስታ አይደለም፡፡ “ሃይማኖትሰ፣ ጥይቅት፣ ይእቲ፣ ለዘይሴፈዋ” ይላታልና ዕብ. 11፥1፡፡ ይህን ለመረዳት እግዚአብሔር ዓይነ ልቡናችንን ያብራልን፡፡ በማስተዋል እየፃፍኩ ነው እናንተም አስተውላችሁ አሜን! በሉ፡፡ ይህ ማለት ሳይገባችሁ እንደ መፈክር በሚያስተጋባ ድምፅ በአሜንታ አጅቡኝ ማለቴ አይደለም፡፡ በማስተዋል አሜን! አላችሁ? እሺ ስለ ሃይማኖት እያወራን ነው፡፡