Saturday, August 8, 2015

ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር

እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ::
ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ መካነ ፍሥሐ ምጡቀ ፤ በአእባነ ባህርይ ዘተነድቀ ፤ ማርያም ደብተራ እንተ ኢትትከደን ሠቀ፡፡ እመቤቴ ማርያም ሆይ ምጡቅና ሩቅ ወደሚሆን የደስታ ቦታ ላረገ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል ፡፡ ይኸውም ኅብሩ ሊመረምሩት በማይቻል ዕንቊ የታነፀ ሕንፃ ይገኝበታል (መልክአ ማርያም)፡፡