Showing posts with label ትምህርት. Show all posts
Showing posts with label ትምህርት. Show all posts

Tuesday, October 17, 2017

እመሰ ረሳዕኩኪ ኢየሩሳሌም ለትርስዓኒ የማንየ መዝ. ፻፴፮ ፥ ፭

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን

ኢየሩሳሌም ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ፡፡

በዲያቆን ዓለማየሁ ሀበቴ

 (ክፍል ፩)

ኢየሩሳሌም  ማለት ሀገረ ሰላም  ማለት ሲሆን ፤ በቅዱስ መጽሐፍ ከነዓን ፣ ምድረ ርስት ፣ የተስፋ ምድር ፣ ማርና ወተት የሚፈስባት ሀገር ፣ የዳዊት ከተማ በመባል ትታወቃለች[1] ፡፡ ኢየሩሳሌም እግዚኣብሔር ለአብርሀምና ለዘሩ ርስት አድርጎ የሰጠው  የተስፋ ምድር ናት ፡፡ እግዚአብሔርም አብራምን አለው ፡- ከአገርህ ፣ ከዘመዶችህም ፣ ከአበትህም ቤት ፣ ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ ፡፡ ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ ፣ እባርክሃለሁ ፣ ስምህንም አከብረዋለሁ ፤ ለበረከትም ሁን ፤ የሚባርኩህንም እባርካለሁ ፣ የሚረግሙህንም እረግማለሁ ፣ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ ፡፡ አብራምም እግዚአብሔር እንደ ነገረው ሄደ ፡፡ ከካራን ወጥቶም ወደ ከነዓን ምድር ገባ ፡፡ እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ አለው ፡፡ ዘፍ. ፲፪ ፥ ፩- ፯ ፡፡

Friday, October 13, 2017

ወርኃ ጽጌ



ጾመ ጽጌ ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ያለው አንድ ወር ከዐሥር ቀን ወይም 40 ቀን ወርኃ ጽጌ፣ ዘመነ ጸጌ፣ ተብሎ ይጠራል፡፡ በነዚህም ቀናት በየቤተክርስቲያኑ የሚነበቡ ምንባባት፣ የሚዘመሩት መዝሙራት፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚቆመው ማኅሌት በጠቅላላው የሚነገረው ስብሐት እግዚአብሔር ሁሉ ሰማይ በከዋክብት ምድር በጽጌያት አሸብርቀው የሚታዩ መሆናቸውን የሚገልጽ ነው፡፡

Wednesday, April 26, 2017

የትንሣኤ በዓል ትርጕሙና አከባበሩ



በሊቀ ትጉሃን ኃይለ ጊዮርጊስ ዳኘ
ሚያዝያ ቀን ፳፻፱ .
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሰን!
«ትንሣኤ» የሚለው ቃል የግእዝ ቃል መገኛውተንሥአ = ተነሣየሚለው ግስ ሲኾን፣ ትርጕሙም መነሣት፣ አነሣሥ፣ አዲስ ሕይወትን ማግኘት ማለት ነው፡፡ትንሣኤበየመልኩ፣ በየዓይነቱ ሲተረጐም አምስት ክፍል አለው፤
የመጀመርያው ትንሣኤ ሕሊና ነው፤ ይህም ማለት ተዘክሮተ እግዚአብሔር (እግዚአብሔርን ማሰብ) ነው፡፡
ሁለተኛውም ትንሣኤ ልቡና ነው፤ የዚህም ምሥጢሩ ቃለ እግዘብሔርን መስማትና በንስሐ እየታደሱ በሕይወት መኖር ነው፡፡
ሦስተኛው ትንሣኤ ለጊዜው (በተአምራት) የሙታን በሥጋ መነሣት ነው፡፡ ነገር ግን በድጋሜ ሌላ ሞት ይከተለዋል፡፡
አራተኛው ትንሣኤ ክርስቶስ በሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጎ መነሣቱን ያመላክታል፡፡ የርእሰ ትምህርታችን መነሻም ይህ ነው፡፡
አምስተኛውና የመጨረሻው የትንሣኤ ደረጃ የባሕርይ አምላክ የጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ መሠረት ያደረገ ትንሣኤ ዘጉባኤ ሲኾን፣ ይህም ከዓለም ኅልፈት በኋላ ሰው ዅሉ እንደየሥራው ለክብርና ለውርደት፣ ለጽድቅና ለኵነኔ በአንድነት የሚነሣው የዘለዓለም ትንሣኤ ነው፡፡

ሰሙነ ትንሣኤ (የትንሣኤ ሳምንት)/በዓለ ኀምሳ


በዲ/ን ዓለማየሁ ሀብቴ
ሚያዚያ ፲፯ ቀን ፳፻፱ ዓ/ም
ከትንሣኤ እሑድ ቀጥለው ያሉት ዕለታትሰሙነ ፋሲካወይምትንሣኤእየተባሉ የሚጠሩ ሲሆን፣ የየራሳቸው ምሥጢራዊ ስያሜም አላቸው፡፡
በዓለ ኀምሳ የሚባለው ከትንሣኤ እስከ በዓለ ጰንጠቆስጤ (በዓለ ጰራቅሊጦስ) ድረስ ያሉት ኀምሳ ዕለታት ናቸው በዚህ ወቅት ቤተክርስቲያን የክርስቶስን ትንሣኤ ታከብራለች በክርስቶም ያገኘችውን ዕረፍተ ነፍስ በምልዓት ትሰብካለች ፡፡ ዕረፍተ መንግሥተ ሰማያትን ታስባለች ፡፡ በነዚህ ዕለታት ዓርብ ረቡዕ አይጾሙም ቀኖና ለተነሳሕያን አይሰጥም ከበደልና ከመበደል ነጻ ሁነን፣ ከበደለኛ አእምሮ ወቀሳ ድነን የምንኖርባት መንግሥቱ በትንሣኤ ትሰጠናለች ፣ በትንሣኤውም በደላችን ሁሉ ሽሯል እንዲሁም በስግደት በድካም በትህርምት የሚኖሩ ሁሉ በዕረፍት በዐለ ኀምሣውን ያሳልፋታል በዚህ ወቅት ቅዳሴ መዝሙር ድካም የማያስከትል ሥርዓተ አምልኮት ይፈጸማል ይህ ሁሉ የሚሆነው በክርስቶስ ዕረፍተ ነፍስ አግኝተናል ጌታ የትንሣኤያችን በኩር ነው እኛም ከተነሣን በኋላ እግዚአብሔር ረኃብ ጥም ድካም ሕማም ፈተና ሞት ፈታኝ መቃብር ብልየት ልደት ልህቀት ኃይለ ዘርዕ ኃይለ ንባብ ኃይለ እንሰሳ የሌለበትን ሥርዓተ ምድር አልፎ በአዲስ ሥርዓተ ሕይወት የምትመራውን ዕረፍተ መንግሥተ ሰማያትን እንወርሳለን ለማለት ሲሆን ቀኖና የማይሰጠው በሥጋም ሆነ በነፍስ ከመበደል ጌታ ነጻ ያወጣናል ባለመበደል በአፋችን ምስጋና መልቶ ሕይወታችን ከበደል ተለይቶ የምንኖርበት ዘመን ይመጣል በትንሣኤው በዕርገቱ ጽድቅና ጸጋ ሕይወት ተሰጥቶናል ከተዋርዶ ነፍስ ድነናል ለማለት ነው በአጠቃላይ ድኅነተ ነፍስ ድኅነተ ሥጋ በኢየሱስ ክርስቶስ ተሰጥቶናል ዕረፍተ መንግሥተ ሰማያት የዘለዓለም ሕይወት ተዘጋጅቶልናል ማለት ነው