በፋሽቶች ይሙት በቃ የተፈረደባቸው ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በችሎት ፊት ለብዙ ሰዓታት ቆመው
ስለዋሉኖ ደከሞአቸው ስለ ነበር ለመቀመጥ ፈልገው ዳኛውን በትሕትናና በፈገግታ ጠየቁት። እንዲ ቀመጡም ፈቀደላቸው፡፡ በመጨረሻም
የሞታቸው ፍርድ ከተነበበ በኋላ የፈረዱባቸውን ዳኞች ጸልየው በመስቀላቸው ባረኩዋቸው። ብፁዕነታቸው እስከ መቃብር አፋፍ ድረስ
የፍርሃትና የድንጋጤ ምልክት ያይደለ ከልብ የሆነ ፍጹም ቆራጥነት ይታይባቸው ነበር፡፡
የሀገራቸው
በጠላት መወረር የሕዝበቸው መገደልና መታስር የቤተ ከርስቲያናቸው መደፈር እስከ ሞት ያደረሳቸው እኒህ እውነተኛ ጳጳስ ለመገደል
ሊወስዱ ጥይት አልፎ ሌላ ስው እንዳይጎዳ ግንብ ይፈለግ ጀመር፡፡ ሩቅ ባለመሔድ ከመካነ ፍትሑ 10 ሜትር ርቆ ግንብ ያለው መግደያ ቦታ ተገኘና ወደዚያ ተወስዱ። ከገዳዮቹም አንዱ ' ፊትዎን ለመሸፈን ይፈልጋሉገ ?' ሲል ጠየቃቸው፡፡ '
ይህ የአንተ
ሥራ ነው ' ሲሉ ብፁዕነታቸው መለሱ ' ፡፡ ከመግደያውም ቦታ እንደ ደረሱ ወንበር ቀረበላቸውና ፊታቸውን ወደ ግንቡ ጀርባቸውን ወደ ሕዝቡ እድርገው
እንዲቀመጡ ሆኑ።