Showing posts with label ጥያቄና መልስ. Show all posts
Showing posts with label ጥያቄና መልስ. Show all posts

Tuesday, January 3, 2017

መጽሐፈ ስንክሳር ምንድን ነው?

ውደ የማኅቶት እድምተኞች፡- ስንክሳር ማለት ምን ማለት ነው?
ስንክሳር የተባለበት ምክኒያት ምንድን ነው? ብለዉ አንድ ጠያቂአችን ለጠየቁት ጥያቄ አጭር ማብራሪያ እነሆ፡፡

መጽሐፈ ስንክሳር አስተጋብአ (ሰበሰበ) ከለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን አስተጉቡእ (ስብስብ) ማለት  ነው ፡፡ ጥርቅምቅም ውጥንቅጥ የተቀያየጠ መድበል የተደባበለ ነገር ማለት ነው ።
የሥላሴን አንድነትና ሦሥትነት÷ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ቅድመ ዓለም ያለእናት ከበሕርይ አባቱ ከአብ÷ ድኅረ ዓለም ያለአባት ከእመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ መወሐዱን÷ የመላእክትን ማዕርግና ሹመት የሚያስረዳ የነቢያትንና የሐዋሪያትን የጻድቃንንና የሰማዕታትን የደናግልንና የመነኮሳትን ምግባር መከራና እረፍት ከዕለት እስካ ዓመት የሚነገር መጽሐፍ ነው፡፡ የቤተ ክሲያንን ታሪክ÷ የመቤታችንን ዜና የልጇንም በጎ ሥራ ኹሉ በሰፊው ይናገራል። ትርጓሜውም በጽርእ የተሰብሰበ ስብስብ ማለት ነው። የቅዱሳን ነቢያትንና ሐዋርያትን÷ የቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታትን÷ ሀይማኖታዊ ተጋድሎ÷ ክርስቲያናዊ ፅናትና ግብር በአጠቃላይ ገቢረ ተአምራታቸውን÷ ገድላቸወንና ትሩፋታቸውን የሚዘክር ዕለተ መታሰቢየቸውንም የ ሚጽሐፍ  መጽሐ ፍ ነው፡፡ ጠቅለል ባለ ቋንቋ መጽሐፈ ስንክሳር ዝክረ ቅዱሳን መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፈ ስንክሳር ከመጻሕፍተ ብሉያትና ሐዲሳት÷ ከገድላትና ድርሳናት የተቀዳ በቤተ ክርስቲያን በየቀኑ የሚነበብ ዜና ቅዱሳን ነዉ፡፡

Sunday, April 10, 2016

ሰማ ሰንበት

ውድ የማኅቶት ታዳሚያን እንደምን ከረማችሁ! ያልገባኝ ጥያቄ ለምንድ ነዉ እኩለ ፆም ሳማ ሰንበት በተለይ የሚከበረዉ? በማለት አንድ የማኅቶት ቤተሰብ ጥያቄ አቅርበዋል:: ውድ ጠያቂአችን ጥያቄዎን በወቅቱ ባለመመለሴ ይቅርታ ይደረግልኝ:: ኔትወርክ የሌለበት ስለነበርኩ ጥያቄውን አላየሁም ነበር:: መልሱን በአጭሩ እነሆ: ሰማ ሰንበት የሚከበረው በዓል ፅላቱ የሰንበት ፅላት ነው:: በምንጃር ወረዳ ሰማ ገዳም የሚከበረው ደግሞ የሰንበት ፅላት (ፅላተ እግዚአ ለሰንበት) የሚገኘው እዚያ ብቻ ስለሆነ ነው:: በእኩለ ጾም በደብረ ዘይት እለት መከበሩ እለቱ የህልፈተ ዓለም መታሰቢያ የምፅአተ ክርስቶስ መዘከርያ እለት ስለሆነ ነው:: ጌታችን ይህን ዓለም ለማሳለፍ ዳግም የሚመጣዉ በወርኃ መጋቢት በእለተ እሁድ በእኩለ ሌሊት ነው:: ይሁን እንጂ ጌታ በማቴዎስ ወንጌል 24: 36 ላይ " ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም።" እንደተናገረው የትኛው ወርኃ መጋቢት የትኛዋ እለተ ሰንበት የትኛይቱ እኩለ ሌሊት እንደሆነ ከእርሱ በቀር አንድም ፍጡር አያውቅም:: ይህ ጌታ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ የዳግም ምፅአቱን ያስተማረውን ትምህርት መሠረት አድርጋ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በዓሉን በዓለ ደብረ ዘይት በዓለ ህልቀተ ዓለም በዓለ ሰንበት በዓለ ዳግም ምፅአት ነገረ ሕይወት ዘለዓለም በማለት ሥርዓት ሠርታ ጊዜ መድባ በዚህች እለት ታከብራለች::

Wednesday, March 16, 2016

የተሳትፎ ጥያቄ


እርስዎም ይሳተፉ፡

እውቀት የማይዘረፍ የማይመዘበር ቋሚ ሀብት ነው፡፡
ሀ. ለመሆኑ እርስዎ ስለእውቀት ምን ያህል ያውቃሉ?
ለ. እውቀት ስንት ደረጃዎች አሉአት? በመንፈሳዊ እይታ ይዘርዝሩ፡፡

Monday, February 1, 2016

አቡነ ኤዎስጣቴዎስ

ውድ ጠያቂያችን ፡- አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ማናቸው? ሰማዕት ናቸው ወይስ ጻድቅ? ብለህ ለጠየቅከው ጥያቄ አጭር መብራርያ እነሆ፡፡ መልካም ንባብ፡፡
ጻድቁ አቡነ ተክለ ሀይማኖትና አቡነ ኤወስጣቴዎስ በመካከለኛው ዘመን የኢትዮዽያ ታሪክ ዕንቁ ሓዋርያት፣ የሀይማኖት አርበኛ ከዋክብት ናቸው፡፡
ኢትዮዽያዊው ሐዋርያ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ያለቸው ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ አባታችን አቡነ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ተወልደው ያደጉት በኤርትራ ክፍለ ሀገር ውስጥ ነው፡፡ አባታችን በ፲፪፷፭ ዓ/ም ገደማ ከአባታቸው ክርስቶስ ሞዓና ከእናታቸው ሥነ ሕይወት ተወለዱ፡፡ የጻድቁ የመጀመሪያ ስም 'ማዕቀበ እግዚእ' (ለጌታ የተጠበቀ) ነበር፡፡ ኤዎስጣቴዎስ የተባሉት በኋላ ነው፡፡ (አቡነ ተክለ ሀይማኖት የመጀመርያ ስም ፍስሃ ጽዮን እንደ ነበር ልብ ይለዋል)፡፡

Friday, December 25, 2015

በእስራኤላውያን የነፃነት ትግል የመቃቢያን ሚና

ጤና ይስጥልኝ የማኅቶት ታዳሚያን እንደምን ዋላችሁ!
ዛሬ እንድ ወዳጄ መቃቢስ ማነው ልጆችስ አሉት ወይ ከሉትስ እነማን ይባላሉ መቃቢያን በእስራኤል የነፃነት ትግል ታሪክ ውስጥ ያለቸውስ ቦታ ምንድን ነው ብለው ለጠየቁኝ ጥያቄ አጭር ማብራርያ እነሆ ብያለሁ፡፡ መልካም ንባብ፡፡
በእስራኤላውያን የነፃነት ትግል የመቃቢያን ሚና
እስራኤል በውጭ ገዢዎች ስልጣን ስር በመውደቅ ረጅም ታሪክ አለት፡፡ መቃቢያንም በዚህ የታሪክ ጉዞ ውስጥ ጉልህ ሚና ነበራቸው፡፡