ጾም ዋጋ የሚያሰጠው ከምግብ በመከልከል
ብቻ ሳይሆን ከኃጢአት ሥራዎችም መራቅ ነው፡፡ ሥጋ በለመብላቱ ብቻ የጾመ የሚመስለው ቢኖር በዚህ አንዳች ነገር አያገኝም፤ ጾሙ
ብላሽ ወይም ከንቱ ናት፡፡ ትጾማለህ? በሥራህ ግለጠህ አሳየኝ፡፡ በምን ዓይነት ሥራ ይገለጣል ትለኝ እንደሆነ ለደሃ ራራለት እዘንለት፡፡
የተጣለህን ታረቀው፣ በባልጄራህ ክብር አትቅና፡፡ መልከ መልካም ሴት ስታይ ውበቷ ሳይማርክህ እለፋት፡፡ ጾም አፍህ ብቻ ሳይሆን
ዐይንህ፣ ጆሮህ፣ አፍንጫህ፣ እግርህ፣ እጅ፣ በአጠቃላይ መላ ሕዋሳትህ መጾም አለባቸው፡፡