በመጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ
ሰው
ብቻ
ማለት
ምንድን ማለት ነው? ብዬ ሳስብ፤ የሚበላ፣ የሚጠጣ፣ በሚለብሰው ልብስ፣ በሚነዳው መኪና የኑሮን ስኬት የሚለካ ማለት ነው። እስከ ሞት የሚኖር ማለት ነው እንደ እንስሳ። ታላቁ ሊቅ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይላል፡፡ ሰው እግዚአብሔር
ሲለየው ጠባዩ እንደ አራዊት፤ አመጋገቡ እንደ እንስሳ፣ ሆኖ መልኩ ብቻ የእግዚአብሔር ሆኖ ይቀራል። በጣም ቀለል ባለ አገላለጽ
ሲም ካርዱ የወጣ ጥሪ የማይቀበል ሞባይል ማለት ነው። ለጉትቻ ማንጠልጠያ ብቻ የተሠራም ጆሮ አለ።