Tuesday, January 5, 2016

እስመ በኀቤኪ ተወልደ ክርስቶስ ዳግማይ አዳም

በዲ/ን ዓለማየሁ ሀብቴ
ታሕሳስ ፳፮ ቀን ፳፻፰ ዓ/ም
ለእንግዶች ማረፊያ ስፍራ ያልነበረሽ የተናቅሽ መንደር፣ የከብቶች ግርግም፣ የእረኞች ማደርያ ታናሽቱ ከተማ ቤተልሔም ሆይ ክርስቶስ ባንቺ ተወልዷልና ደስ ይበልሽ፡፡ ውርደት ንቀትሽ ቀርቶ፤ ታናሽነትሽ ተረስቶ ታላቅ አደባባይ የክብር ዙፋን ሆነሽ ተገኝተሸል፡፡