ጻድቁ አቡነ ተክለ ሀይማኖትና አቡነ ኤወስጣቴዎስ በመካከለኛው ዘመን የኢትዮዽያ ታሪክ ዕንቁ ሓዋርያት፣ የሀይማኖት
አርበኛ ከዋክብት ናቸው፡፡
ኢትዮዽያዊው ሐዋርያ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ያለቸው ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ አባታችን
አቡነ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ተወልደው ያደጉት በኤርትራ ክፍለ ሀገር ውስጥ ነው፡፡ አባታችን በ፲፪፷፭ ዓ/ም ገደማ ከአባታቸው ክርስቶስ ሞዓና ከእናታቸው ሥነ ሕይወት
ተወለዱ፡፡ የጻድቁ የመጀመሪያ ስም 'ማዕቀበ እግዚእ' (ለጌታ የተጠበቀ) ነበር፡፡ ኤዎስጣቴዎስ የተባሉት በኋላ ነው፡፡ (አቡነ ተክለ ሀይማኖት የመጀመርያ ስም ፍስሃ
ጽዮን እንደ ነበር ልብ ይለዋል)፡፡
አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ገና ከልጅነታቸው መንፈሰ እግዚአብሔር ያደረባቸው ስለሆኑ ለዚህ ዓለም ግድ አልነበራቸውም:: ከቤተ ክርስቲያን መገብት መምህራን
የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ተምረው ዲቁና ተቀብለው በነቅንነትና በቅድስና ሲያገለግሉ አበው ደግማዊ እስጢፋኖስ ብለው ይጠሩአቸው
ነበር፡፡ ጻድቁ ገና በወጣትነት እድሜአቸው ምናኔን መርጠው: በጾም፣ በጸሎትና በስግደት ይተጉ
ጀመር፡፡ እንዲህ ባለ ሕይወት ሳሉ አንድ ቀን ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ዘንድ መጣ:: በዘባነ ኪሩብ: በግርማ ቢያዩት ደነገጡ:: ጌታ ግን ወዳጄ ኤዎስጣቴዎስ ገና ከእናትህ ማሕጸን መርጬሃለሁ:: ከኢትዮዽያ እስከ አርማንያም ሐዋርያ ትሆን ዘንድ ሹሜሃለሁ:: ሐዋርያው ቅ/ጳውሎስን ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእስራኤልም
ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ብሎ በጠራው አጠራር ጠራቸው፡፡ የሐዋ. ፱፥ ፲፭፡፡ ዘኪያከ ሰምዐ ኪያየ ሰምዐ (አንተን የሰማ እኔን ሰማ አንተን እንቢ ያለ እኔን እንቢ አለ ብሏቸው ባርኩዋቸው ዐረገ:: የሚሰማችሁ እኔን ይሰማል፥ እናንተንም
የጣለ እኔን ይጥላል፤ እኔንም የጣለ የላከኝን ይጥላል እንዲል ሉቃ. ፲፥ ፲፮።
ጻድቁ አባታችን ስለ ቸር ስጦታው ፈጣሪያቸውን አመስግነው ቅስናን ተቀብለው እንደ ሐዋርያት ቅዱስ ወንጌልን መስተማር ጀመሩ:: ስም ዝናቸው ፈጥኖ በመላ ሀገሪቱ ተሰማ:: በየቦታው እየተዘዋወዞሩ አሕዛብን አሳምነው እያጠመቁ፣ ያመነውን በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እያጸኑ፣ ገዳማው ሕይወትን እያስፋፉ ኖሩ:: በታላቁ ገዳማቸው በርካታ አርድእትን አስተምረው አፍርተዋል:፡ ጻድቁ አባታችን ቀደሚት ሰንበት
ልክ እንደ ሰንበት ክርስቲያን (እሁድ ሰንበት) እንዲትከበር እስከ ስደት ድረስ ከፍተኛ ተገድሎ አድርገዋል፡፡ ዓላማቸውንም አሰክተዋል፡፡
በመጨረሻ ሕይወታቸውም በገዳማቸው ላይ ደቀ መዝሙራቸው አባ አብሳዲን ሹመው ለአዲስ በወቅቱ በነበረው ችግር ለስደት ተነሱ:: ልጆቻቸው በገደማቸው
እንዲጸነ መክረው ተወሰኑትን አስከትለው
ወደ አርማንያ ተጓዙ:: በመንገድም ወደ ባሕረ ኢያሪኮ ሲደርሱ የሚሻገሩበት መርከብ አጡ:: ድንቅ አባት ናቸውና በእምነት አጽፋቸውን (መጎናጸፊያቸውን) አውልቀው ባሕሩ ላይ ጣሉት:: በትእምርተ መስቀል አማትበው ተቀመጡበት:: ደቀ መዛሙርቶቻቸውም ባሕሩ ላይ በተነጠፈው መጎናጸፊያ ላይ ከበው ተቀመጡ:: ከሰማይም ጌታችን ወርዶ በመካከላቸው ቆመ:: ቅ/ሚካኤል በቀኝ ቅ/ገብርኤልም በግራ ቆሙ:: ጻድቁ ደግሞ ልጆቻቸውን ያስተምሯቸው ይተረጉሙላቸውም ጀመሩ:: በመካከል ግን አንዱ ደቀ መዝሙራቸው (የማነ ብርሃን የተባለ) በቅኔ ቤት በመጠራጠሩ እርሱ የተቀመጠባት ብቻ ተቀዳ ሰጥሞ ሞተ:: ጻድቁ አባታችን ከሰጠመበት አውጥተው ከሞት አስነስተውታል:: በዚህም ምክንያት 'ዘአደወ ባሕረ' (ማዕበልን የተሻገረ) ተብለዋል:: አቡነ ኤዎስጣቴዎስ በአርማንያ ለዘመናት ቅ/ወንጌልን ሰብከው፣ ሕይወተ ገዳምን አስፋፍተው፣ ብዙ ተአምራትን ሠርተው ከዚህ ዓለም በክብር
አልፈዋል፡፡
በረከታቸው ይደርብን፡፡
No comments:
Post a Comment