አልጋህን ተሸክመህ ሂድ፡:
አራተኛው እሁድ መጻጉዕ ይባላል፡፡ መጻጉዕ ማለት በሽተኛ ማለት ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕበራይስጥ ቤተ ሳይዳ ወደምትባል አንዲት መጠመቂያ ወርዶ በልዩልዩ ደዌያት የተያዙ ብዙ ሕሙማንን መፈወሱ የሚወሳበት፣ የሚዘመርበት ሳምንት ነው፡፡ በተለይም ለሰላሳ ስምንት ዓመታት በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ ተይዞ የነበረው አንድ ሕሙም በጌታ ቃል ተፈውሶ አልጋውን ተሸክሞ ወደ ቤቱ መሄዱ በቅዱስ መጽሓፍ በጉልህ ተመዝግቧል፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ሳምንት ወደ ቤተሳይዳ መጠመቂያ ወርዶ አንካሶችን
አቀና፣ ለምጻሞችን አነፃ፣ እውራንን አበራ፣ በሎሎችም ልዩ ለዩ ደዌ የተያዙትን በጣም ብዙ ሕሙማንን ፈወሰ፡፡ ሕሙማኑ በቤተ ሳይዳ
መጠመቂያ የተሰበሰቡት ድህነትን ፍለጋ ነው፡፡ ዛሬ ደዌ የፀናበት በሽታ የበረታበት ከበሽታው ለመዳን ከሕማሙ ለመፈወስ ወደ ጠበል
እንደሚሄድ በዘመነ ብሉይ የእግዚአብሔር መልአክ በሰምንት አንድ ቀን ወደዚያች መጠመቂያ ገብቶ ውሃውን ሲያናውጥ ቀድሞ ወደ መጠመቂያይቱ
የገባ ከማናቸውም ከለበት ደዌ ሁሉ ይድን ይፈወስ ነበር፡፡ እለቷም ቀደሚት ሰንበት (ሰንበተ አይሁድ) ነበረች፡፡ ፈውስ መሰጠቱ
በአባቶቻችን ዘመን ነበር እንጂ በእኛስ ዘመን እግዚአብሔር ትቶናል እንዳይሉ ነው፡፡ በውሃው ተጠምቆ የሚፈወሰው አንድ ሰው ብቻ
መሆኑ ደግሞ በዘመነ ብሉይ ፍጹም ድህነት አለመኖሩን ያጠይቃል፡፡ ፍጹም ድህነት የተገኘው በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ
ነው፡፡ በልዩ ለዩ ደዌያት ተይዘው በቤተ ሳይዳ ተኝተው የውሃውን መናወጥ ከሚጠባበቁ ሕሙማን መካከል በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ ተይዞ
ለሰላሳ ስምንት ዓመታት በዚያ የተኛ ደዌው የጸናበት አስተማሚ ጠያቂ ዘመድ የሌለው አንድ ሰው አገኘ፡፡ ይህ ሰው ከደዌው ጽናት
የተነሳ መጸጉዕ ተባለ፡፡ መጸጉዕ ማለት ሕሙም ድውይ ማለት ነው፡፡ ሳምንቱም መጸጉዕ ተብሎ በእርሱ ተሰይሟል፡፡ ጌታችንም ወደ እርሱም
ቀርቦ ልትድን ትወደለህን ብሎ በሽተኛውን ጠየቀው፡፡ መጠየቁ ሰውየው መዳን እንደሚፈልግ ሳያውቅ ቀርቶ ሳይሆን በእለተ አርብ ፈውሰኝ
ሳልል ፈውሶኛል ብሎ የሚመሰክርበት ነውና አስፈቅዶ ለማዳን ጠየቀው፡፡ አንድም በድህነት ውስት ሰው የራሱ ሱታፌ እንዳለው ለማስተማር
ነው፡፡ ድውዩም ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለሰለት። ቸሩ አምላካችን ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው። መጸጉዕም ጉልበቴን ቁርጩምጩሚቴን ሳይል ጉልበቱ ጸንቶ ተነሳ አልጋውንም ተሸክሞ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ ፈርሳውያን
ግን በሰንበት አልጋህን ተሸክመህ መሄድ እትችልም፣ ፈውስም በሰንበት መሆን የለበትም ብለው ተቆጡ፡፡ ዮሐ. ፭፥ ፩– ፱፡፡
እኛም በለን አቅም በነፍስ በሥጋ
የተቸገሩትን ሁሉ መርዳትና ማገዝ እንደለብን የምንማርበት ሳምንት ነው፡፡ ሕሙማንን መጠየቅ፣ የተሰሩትን መገብኘትና ማስፈታት፣ የተራቡትን
ማጉረስ፣ የተጠሙትን ማጠጣት፣ የታረዙትን ማልበስ ያዘኑትን ማረጋጋት ከጌታችን የተማርናቸው ክርስቲያናዊ ተግባራት ናቸው፡፡ እንደ
ጸሓፍት ፋርሳውያን እግዚአብሔር በቸርነቱ የጎበኛቸውን አንቃወም፡፡ መልካም በተደረገላቸው፣ በለስ በቀናቸውና ገመድ ባማረ ስፍራ
በወደቀችላቸው አንቅና፡፡ በወንድሞቻችን ደስታ እንደሰት፤ በሀዘናቸውም እናጽናናቸው፡፡ በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ ለተያዙትን እንጸልይላቸው፣
በደዌ ነፍስ (በኃጢአት) የወደቁትን አንስተን ወደ መጠመቂያይቱ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንጨምራቸው፣ ብቸንነት ተሰምቶአቸው
ወገን ዘመድ ሰው የለንም ለሚሉት ሰው ሆነን ከጎናቸው በመገኘት የተኙበትን የችግር አልጋ ተሸክመው እንዲሄዱ እንርዳቸው፡፡ የማይቆረቁር
ምቹ አልጋ ሕገ እግዚአብሔር ነውና ምቾተ ነፍስ አጥተው ሰላመ አእምሮ አጥተው በችግር እመም የሚሰቃዩትን ሁሉ አልጋችሁ ሕገ እግዚአብሔርን
በመትከፈ ልቡናችሁ ተሸክማችሁ ሂዱ እንበላው፡፡
የቤተ ክርስቲያን ልማቷ (ፕሮጀክቷ)
በሰው ልብ ላይ ነውና በተግባራችን፣ አነጋገራችን፣ በአኗኗራችን ለሰዎች ቀናውን መንገድ ማሳየትና በድከማቸው ሁሉ ማገዝ የሳምንቱ
የማኅቶት መልእክት ነው፡፡
የእለቱ መዝሙር ፡- አምላኩሰ ለአዳም
ምስባክ ፡- እግዚአብሔር ይረድዖ
ውስተ ዓራተ ሕማሙ፡፡ ወይመይጥ ሎቱ ኩሎ ምስካቢሁ እምደዌሁ አንሰ እቤ እግዚኦ ተሰሐለኒ፡፡ መዝ. ፵(፵፩) ፥ ፫ - ፬
ወንጌል ፡- ማር. ፪ ፥ ፩ -
፲፪
No comments:
Post a Comment