ለብሉይ ሰውነታችን ሕዋሳትን ሁሉ
እየቃኘ በበጎ ሥራ የሚያውቸው እንደ ንጉሥ የሚያዝ ልቡና አለው፡፡ ያለ ልቡና መሪነት ሕዋሳት ሁሉ ምንም ለሠሩ አይችሉም፡፡ ስለዚህ
ልቡና የሌለው ሰው እብድ ዝንጉዕ ይባላል እንጂ ሕያው ሰው አይባልም፡፡
እንደዚሁም ለሐዲሱ ሰውነታችን
ሥራዎቹን የሚያከናውንበት የሥራ መሪው ጾም ነው፡፡ ያለ ጾም መሪነት ምንም በጎ ሥራ ሊሠራ አይችልም፡፡ ይህንንም ወደ ሌላ ሳንሄድ
በልተን ጠጥተን በጠገብን ጊዜ የሚሰማን ስሜትና በምንጾበት ወራት የሚሰማን ስሜት ብናመዛዝነው ልንረዳው እንችላለን፡፡