ውድ አንባቢያን ሸክማችሁ
የከበደ ደካሞች ሁሉ ወደ እኔ ኑ
በሚል
ርእስ በሁለት
ተከታታይ ክፍል ያቀረብኩላችሁን ስብከት የመጨረሻውን ሶስተኛ ክፍል እነሆ፡፡ መልካም ንባብ::
ስለዚህ
አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፃማ ሓጢአት የደከማችሁ፣ፃዕረ ሞት የከበዳችሁ፤ያስመረራችሁ የሰው ልጆች ሁሉ
በሕግ፣በአምልኮ፣በምግባር፣በንስሓ ወደ እኔ ኑ፣ቅረቡ እኔም በፍቅሬ አሳርፋችኋለሁ፣ሸክማችሁንም አቀልላችኋለሁ፡፡ወንጌል፣መስቀለ
ሰላም፣ፍቅር ቀንበሬን ተሸከሙ እረፍተ ሥጋ እረፍተ ነፍስ ታገኛለችሁ፡
፡ሰማያዊት ርስት መንግሥተ ሰማያትን ትወርሳላችሁ ብሎ
ሰውን ሁሉ በፍቅር፣በረድኤት ወደ ራሱ ጠራ፡፡ጌታችን የፍቅር የሰላም አምላክ ነውና‹‹እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ
እኔ ኑ፡፡እኔም አሳርፋችኋለኁ የዓለምን ግሳንግስ ከባድ ሸክም ጥላችሁ ቀሊሉንና ልዝቡን ቀንበሬን ተሸከሙ››አለ፡፡ያምላካችን ቀንበር
ቀላልና ምቹ ነው ፡፡ አይከብድም ፤ አይጎረብጥምም ፡፡ ዓለም የምታሸክመን ቀንበር ግን ክቡድ ነው ፡፡ አይማችም ፣ ይቆረቁራል
፣ ያሰለቻል ፣ ያደክማልም ፡፡ ጦርነቱ ፣ ጥላቻው ፣ ዝሙቱ ፣ መለያየቱ ፣ ወዘተ ጥሎት የሚሄደው ጠባሳ አለ ፡፡ የሚያም ፣ የሚያብከነክን
፣ የሚያቆዝም ሸክም ቁስለ ህሊናን ጨምሮ ሰላም የሚነሳ ነው፡፡የጌታችን ቀንበር ግን ምቹና ለስላሳ ነው፡፡ቀንበሩ ፍቅርና ሰላም
ነው ፡፡ ክፋት ፣ ምቀኝነት ፣ ተንኮል ፣ ቅንአት ፣ ሴሰኝነት ፣ ጥላቻ ፣ ግድያ ፣ የሌለበት ፣ ፍቅርና ሰላም የነገሠበት
ስለሌላው መሞት መጠወተ ርእስ ያለበት የደስታ ሕይወት ነው ፡፡
ውድወገኖቼ፡-ይህ ጥሪ የሕይወት ጥሪ ነው፡፡ጥሪው ለሁሉም የሰው ዘር ነው፡፡
ጎሳን፣ብሔርን፣ጎጥን፣ጾታን፣ወዘተ አይለይም፡፡ጥሪው መልካም አድራጊዮችን ብቻ ሳይሆን ክፉ አድራጊዎችንም ይጨምራል፡፡ሁላችንም
በዘለዓለማዊው ንጉሥ ወደ ዘለዓለም ሕይወት ተጠርተናል፡፡ለልጁ ሠርግ የደገሰውን ንጉሥ ጥሪ እናስታውስ፡፡ ማቴ.፳፪÷፱-፲…እንግዲህ
ወደ መንገድ መተላለፊያ ሄዳችሁ ያገኛችሁትን ሁሉ ወደ ሠርጉ ጥሩ አለ፡፡እነዚያም ባሮች ወደ መንገድ ወጥተው ያገኙትን ሁሉ
ክፉዎችንም በጎዎችንም ሰበሰቡ፡፡የሠረጉም ቤት ተቀማጮች ሞሉት፡፡
እኛስ
ከሠርጉ ቤት ገብተናል?ወይስ ገና ውጭ ንን?በሠርግ ቤት ደስታ፣ፍቅር ከሁሉም በላይ ሁሉን የሚያስደስት ሙሽራ አለ፡፡ስለዚህ
ሁሉን የሚያስደስት ሰማያዊ ሙሽራ ወደ አለበት ወደ አስደሳቹ የክርስትና ሕይወት ተጠርተናልና ሸክማችንን ቶሎ በንስሓ አራግፈን
ወደ ሠርጉ ቤት እንግባ፡፡መጠራታችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ ተብለናልና፡፡
ስለዚህ
ወንድሞች ሆይ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፡፡፪ጴጥ.፩÷፲፡፡
የዛሬዋም
ዓለም ክርስቶስ ሲመጣ የነበረችውን ዓለም ትመስላለች ፡ ፡እንደ ያኔው ሁሉ ዛሬም ትርምስምሷ በዝቷል ፡፡ ኃጢአቷ በርክቷል ፡፡
አዎ !
ዛሬም ገሀብ ፣ ቸነፈር ፣ በሽታ ፣ ሽብር ፣ ጦርነት ፣ ስደት ፣ መከራ ፣ ችግር ፣ ሱሰኝነት
፣ አመንዝራነት ፣ ምቀኝነት ፣ ቡድንተኝነት ፣ ተንኮል ፣ ወዘተ ነግሷል ፡፡ ብዙ ማህበራዊና መንፈሳዊ ቀውሶች በዓለም ላይ
በዓለም ላይ ይስተወላሉ ፡፡ ይህ ሁሉ ለሀገር ፣ ለወገን ፣ ለቤተ ክርስቲያን ፈተና ነው ፡፡ ለሁላችንም ማህበራዊና መንፈሳዊ
ሕይወት እጅግ በጣም ፈታኝና ከባድ ሸክም ነው፡፡ብዙ የመከፋፈል ሸክሞች አሉ ፡፡ በዘር ፣ በጎሳ ፣ በቋንቋ የመለያየት ሸክም ፡፡
በሀይማኖት ስም የራስን ክብርና ዝና የመናኘት ክፉ ልምድ ሕዝቡን የሚያስጨንቁ ከባድ ሸክሞች ኛቸው፡፡ይህ ሕዝብ ሸክሙን
የሚያቀልለትን ወገን ይፈልጋል፡፡አኛ አሁን ይህን ቃል የምንማረው አገልጋዮችና ሁላችን ክርስቲያኖች በመጀመሪያ የራሳችንን ሸክም
በንስሓ አስወግደን ይህን ግራ የተጋባውን ዓለም የማገዝ፣የመርዳት ብሎም የመታደግ ኃላፊነት አለብን፡፡ሸክሙን የሚያራግፍበትን
ቦታ መምራትና ማሰሳት ይገባናል፡፡ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ሁሉ ሸክም ለማራገፍ ነው ሰውን ወደ ራሱ
የጠራውን የንስሓ ጥሪ መስተጋባት ይጠበቅብናል፡፡በደለኛው በንስሓ የኃጢአት ሸክሙን እንዲያራግፍ፣ሕመምተኛው
እንዲፈወስ፣በለአደራው የተጣለበትን ሀላፊነት ተወጥቶ ለሽልማት እንዲበቃ መክሊታችንን መመንዘር ይኖርብናል፡፡ማቴ.፳፭፥፲፬-፴
ይህን
ከባድ ሀላፊነት ለመወጣት በጀመሪያ እኛ የተጫነንን የጎጠኝነት፣የጠባብ ብሔርተኝነት፣የትዕቢት፣የንዝህላልነት፣የዘማዊነት፣የጥላቻ
ሸክማችንን ሁሉ ማስወገድ አለብን፡፡አለበለዚያ እንኳን የሌላውን ሸክም ልናቀል ቀርቶ የራሳችንን መሸከም ያደግተናል፡፡
ስለዚህ
ዛሬውኑ ንስሓ እንግባ፣ወገባችንን አጥብቀን እንታጠቅ፣መብራታችንም ይበራ፡፡የሰዎችን (የደካሞችን) ሸክም ለማቃለል ዛሬ
የራሳችንን ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ወደ ክርስቶስ ቀርበን እናራግፍ፡፡የዓለምን አሻንክታብና ግሳንግስ አስወግደን የፅድቅና የጦር
ዕቃ ፍቅርን እንልበስ፡፡ያኔ ብርሃናችን በሰው ሁሉ ፊት ደምቆ ይበራል፡፡የሕይወት ፋናም ይሆንላቸዋል፡፡
ለዚህች
አልጫ ዓለም ማጣፈጫ ጨው፣የኑሮ ቅመም፣የሕይወት ብርሃን ሆንን ዓለሙን ከጥፋት ጎዳና እንታደግ፡፡ጨው ናችሁ፣ብርሃን ናችሁ
ተብለናልና፡፡ማቴ.፭፥፲፫-፲፮፣ሮሜ.፪፥፲፯-፳፬፡፡ለዚህ ታላቅ፣ቅዱስና ክቡር ዓላማ እንድንበቃ ወደ ክስርስቶስ ቀርበን
ሸክማችንን በንስሓ ማራገፍና ከድካማችን ሁል ማረፍ ያስፈልገናል፡፡ሓዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም እንዲህ ብሎ ይመክረናል፡-አኛ ደግሞ
ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአትአስወግደን የእምነታችንን ራስና ፈፃሚውን ኢየሱስን ተመልክተን በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግስት
እንሩጥ፡፡ዕብ.፲፪፥፪፡፡
ማጠቃለያ፡-የዚህ ትምህርት ዕምብርቱ፣ማዕከሉ የንስሓ ትምህርት
ነው፡፡ጌታችን ከላይ በርእሱ ባየነው ኃይለ ቃል ያስተላለፈው ጥሪ የንስሓ ጥሪ ነው፡፡ንስሓ ደግሞ ከሰው ልጆች ጋር ለመታረቅ የተዘረጋች
የእግዚአብሔር የምህረት እጅ ናት፡፡ስለዚህ ሁላችን በዚህ በእግዚአብሔር የምህረት እጅ ለመዳሰስና የኃጢአት ሸክማችንን ለማራገፍ
ለንስሓ እንሽቀዳደም፡፡
ወስብሐት
ለእግዚአብሔር
No comments:
Post a Comment