Monday, April 20, 2015

ሸክማችሁ የከበደ ደካሞች ሁሉ ወደ እኔ ኑ፡፡ ማቴ.፲፩÷፳፰ ክፍል ሶስት

ውድ አንባቢያን ሸክማችሁ የከበደ ደካሞች ሁሉ ወደ እኔ ኑ በሚል ርእስ በሁለት ተከታታይ ክፍል ያቀረብኩላችሁን ስብከት የመጨረሻውን ሶስተኛ ክፍል እነሆ፡፡ መልካም ንባብ::
ስለዚህ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፃማ ሓጢአት የደከማችሁ፣ፃዕረ ሞት የከበዳችሁ፤ያስመረራችሁ የሰው ልጆች ሁሉ በሕግ፣በአምልኮ፣በምግባር፣በንስሓ ወደ እኔ ኑ፣ቅረቡ እኔም በፍቅሬ አሳርፋችኋለሁ፣ሸክማችሁንም አቀልላችኋለሁ፡፡ወንጌል፣መስቀለ ሰላም፣ፍቅር ቀንበሬን ተሸከሙ እረፍተ ሥጋ እረፍተ ነፍስ ታገኛለችሁ፡