ዶሮ ናት፡፡ ባለቤቶቿና ጎረቤቶቿ
ያሰጡትን ስጥ በልቼ ባልጨርስ ጭሬ ልጨርስ አለች፡፡ በልታ የማትጨርሰውን ስጥ መበተን፣ ትንሽ ተጠቅማ ብዙ ማጥፋት ወደደች፡፡
ቅዱስነታቸው ላይጠቅም ላይረባቸው
ሀገርን በሚጎዳ የቤተ ክርስቲያንን ሕልውና በሚፈታተን፤ በሰውም ሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ ክብርና ሞገስ ላያገኙበት የቤተ ክርስቲያን
ልጆችን በሚያስከፋ፣ ቅን አገልግሎታቸውን በሚያደናቅፍ አደገኛ ሥራ ተጠምደው ሳያቸው የዶሮዋ አባባል ትዝ አለኝ፡፡
ቤተ ክስቲያን የምትገለገልበትን እግዚአብሔርም የሚከብርበትን በአበው ቤተ ክርስቲያን
በፅኑዕ መሠረት ላይ የተመሠረተውን የአገልግሎት ማሕበር ለማፍረስ፣ ያለ ደመወዝ በፀጋ የሚያገለግሉትንና የሚገለገሉትን አእላፍ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ለመበተን ቆርጠው ተነስተዋል፡፡ የገዛ ልጆቻቸውን
በጠላትነት ፈርጀው እስከ መጨረሻው ድረስ ለመታገልም ወስነዋል፡፡ አስከ ሞት ድረስ እታገላለሁ ብለዋል፡፡