Wednesday, April 13, 2016

«ስለምን ጾምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም?»/ኢሳ. ፶፰፥፫/



በቀሲስ  ስንታየሁ አባተ
በኢሳይያስ ዘመን የነበሩ እስራኤላውያን የተናገሩት ቃል ነው። እስራኤላውያን የሚጾሟቸው ብዙ አጽዋማት ነበሯቸው። ለምሳሌ ያህልም ብናይ በሳምንት ሁለት ጊዜ በሳምንት ሁለት ቀን ይጾሙ እንደነበር በሉቃ. ፲፰፥፲፪ ላይ ያለው ቃል ያስረዳል። ማክሰኞና ሐሙስ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ወደ ደብረ ሲና የወጣበትና ከዚያ የወረደበት ዕለት ለማሰብ እስራኤላውያን በሳምንት ሁለት ቀኖች ይጾሙ ነበር። በነቢዩ በዘካርያስ ትንቢትም ላይ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን እንዲህ ብሎ አዝዟቸዋል «የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአሥረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሀሤትም በዓላት ይሆናል ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ወደዱ።» ተብሎ ለእስራኤላውያን ከእግዚአብሔር ዘንድ በነብዩ በኩል በተነገራቸው መሠረት የተጠቀሱትን ይጾሙ ነበር። /ዘካ. ፰፥፲፰-፲፱/

Sunday, April 10, 2016

ሰማ ሰንበት

ውድ የማኅቶት ታዳሚያን እንደምን ከረማችሁ! ያልገባኝ ጥያቄ ለምንድ ነዉ እኩለ ፆም ሳማ ሰንበት በተለይ የሚከበረዉ? በማለት አንድ የማኅቶት ቤተሰብ ጥያቄ አቅርበዋል:: ውድ ጠያቂአችን ጥያቄዎን በወቅቱ ባለመመለሴ ይቅርታ ይደረግልኝ:: ኔትወርክ የሌለበት ስለነበርኩ ጥያቄውን አላየሁም ነበር:: መልሱን በአጭሩ እነሆ: ሰማ ሰንበት የሚከበረው በዓል ፅላቱ የሰንበት ፅላት ነው:: በምንጃር ወረዳ ሰማ ገዳም የሚከበረው ደግሞ የሰንበት ፅላት (ፅላተ እግዚአ ለሰንበት) የሚገኘው እዚያ ብቻ ስለሆነ ነው:: በእኩለ ጾም በደብረ ዘይት እለት መከበሩ እለቱ የህልፈተ ዓለም መታሰቢያ የምፅአተ ክርስቶስ መዘከርያ እለት ስለሆነ ነው:: ጌታችን ይህን ዓለም ለማሳለፍ ዳግም የሚመጣዉ በወርኃ መጋቢት በእለተ እሁድ በእኩለ ሌሊት ነው:: ይሁን እንጂ ጌታ በማቴዎስ ወንጌል 24: 36 ላይ " ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም።" እንደተናገረው የትኛው ወርኃ መጋቢት የትኛዋ እለተ ሰንበት የትኛይቱ እኩለ ሌሊት እንደሆነ ከእርሱ በቀር አንድም ፍጡር አያውቅም:: ይህ ጌታ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ የዳግም ምፅአቱን ያስተማረውን ትምህርት መሠረት አድርጋ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በዓሉን በዓለ ደብረ ዘይት በዓለ ህልቀተ ዓለም በዓለ ሰንበት በዓለ ዳግም ምፅአት ነገረ ሕይወት ዘለዓለም በማለት ሥርዓት ሠርታ ጊዜ መድባ በዚህች እለት ታከብራለች::

Friday, April 8, 2016

የምንፈልገው ኦርቶዶክሳዊ ወጣት



ከብፁዕ አቡነ ሙሳ
   (የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተ ክርስቲያን የወጣቶች ጉዳይ ጳጳስ)
በለብ ለብ ክርስቲያንና በኦርቶዶሳዊ ክርስቲያን መካከል ትልቅ ልዩነት አለ ምክንያቱም ኦርቶዶክስ ማለት ርቱዕ በሃይማኖቱ ርቱዕ በምግባሩ ነውና።
ኦርቶዶክስ የሚለው ቃል የግሪክ ሲሆን ኦርቶ”  ማለት የቀና የተስተካከለ ርቱዕ ማለት ሲሆን፤ ዶክስማለት ደግሞ ሃይማኖት ማለት ነው። ኦርቶዶክስ ማለትም የቀና  የተስተካከለ ርቱዕ የሆነ ሃይማኖት ማለት ነው።

Friday, March 25, 2016

በልቼ ባልጨርስ ጭሬ ልጨርስ



ዶሮ ናት፡፡ ባለቤቶቿና ጎረቤቶቿ ያሰጡትን ስጥ በልቼ ባልጨርስ ጭሬ ልጨርስ አለች፡፡ በልታ የማትጨርሰውን ስጥ መበተን፣ ትንሽ ተጠቅማ ብዙ ማጥፋት ወደደች፡፡
ቅዱስነታቸው ላይጠቅም ላይረባቸው ሀገርን በሚጎዳ የቤተ ክርስቲያንን ሕልውና በሚፈታተን፤ በሰውም ሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ ክብርና ሞገስ ላያገኙበት የቤተ ክርስቲያን ልጆችን በሚያስከፋ፣ ቅን አገልግሎታቸውን በሚያደናቅፍ አደገኛ ሥራ ተጠምደው ሳያቸው የዶሮዋ አባባል ትዝ አለኝ፡፡
 ቤተ ክስቲያን የምትገለገልበትን እግዚአብሔርም የሚከብርበትን በአበው ቤተ ክርስቲያን በፅኑዕ መሠረት ላይ የተመሠረተውን የአገልግሎት ማሕበር ለማፍረስ፣ ያለ ደመወዝ በፀጋ የሚያገለግሉትንና የሚገለገሉትን  አእላፍ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ለመበተን ቆርጠው ተነስተዋል፡፡ የገዛ ልጆቻቸውን በጠላትነት ፈርጀው እስከ መጨረሻው ድረስ ለመታገልም ወስነዋል፡፡ አስከ ሞት ድረስ እታገላለሁ ብለዋል፡፡

Thursday, March 24, 2016

ዐቢይ ጾምና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ አምልኮ



ክፍል አንድ
 በመምህር ሙሴ ኃይሉ
በተለያዩ መጻሕፍት እንደተጻፈውና በተለያዩ የቤተክርስቲያናችን መምህራን ሊቃውንት በየዓውደ ምሕረቱ ዘወትር እንደሚተነተነው ጾም ማለት በታወቀ፣ በተወሰነ፣ በተቀመረ... ጊዜ ከመብል ከመጠጥ መከልከል፣ መቆጠብ፣ መወሰን... ማለት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን "ጾም" ከክርስቲያናዊ ምግባርና ትሩፋት የሚመደብ ኣስተምህሮ ነው፡፡ ጾም የተመሠረተውም ሆነ የታዘዘው ከፈጣሬ ሰማያት ወምድር ከእግዚአብሔር ነው፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ምዕመን ጾምን በመከተል ለሠራዔ ጾም (ጾም ለሠራለት) አምላክ እየተገዛ፣ እያመለከ፣ እያከበረ፣ እየታዘዘ... በበጎ ሕሊና ተሞልቶ ፈቃደ ሥጋውን (ትዕቢት፣ ስስት፣ ዝሙት፣ ቅንዓት...) ለፈቃደ ነፍሱ (የዋህነት፣ በጎነት፣ ርህሩህነት...) በማስገዛት በፈጣሪ መመሪያ፣ ትእዛዝ እና ፈቃድ መኖር ማለት ነው፡፡

Thursday, March 17, 2016

መልካሙ እረኛ ክርስቶስ


መልካም እረኛ እኔ ነኝ፡፡ የእራሴ የሆኑትን አውቃቸዋለሁ፤ እወዳቸውማለሁ፤ እነርሱም ያውቁኛል፡፡ በግልጽ ቋንቋ የሚወዱኝ ይከተሉኛል፤ እውነትን የማይወድ ግን እኔን አያውቀኝም፡፡
ውድ ወንድሞቼ፡- እናንተም ፈተና እንዳለባችሁ ጌታችን እንዴት ባሉ ቃለት እንደገለጸ እዩ፡፡

Wednesday, March 16, 2016

የተሳትፎ ጥያቄ


እርስዎም ይሳተፉ፡

እውቀት የማይዘረፍ የማይመዘበር ቋሚ ሀብት ነው፡፡
ሀ. ለመሆኑ እርስዎ ስለእውቀት ምን ያህል ያውቃሉ?
ለ. እውቀት ስንት ደረጃዎች አሉአት? በመንፈሳዊ እይታ ይዘርዝሩ፡፡

Tuesday, March 8, 2016

ጾም መድኃኒት ናት (በቅ/ዮሐንስ አፈወር)

ጾም መንፈሳዊ አዝመራ ነው፡፡ በዚህ ወቅት እንደ ወታደር ትጥቃችንን አጥብቀን፣ እንደ ገበሬ መጭዳችንን ስለን፣ ከብኩን ዓለማዊ ከንቱ ምኞት ማዕበል ለመዳን እንደ መርከበኛ የሃሳብ ማሃልቃችንን አጥብቀን እንደ ተጓዥ መንገዳችንን አስተካክለን ወደ መንግሥተ ሰማያት እንገስግስ፡፡ እንቅፋት፣ አባጣ ጎባጣ፣ እሾህ ጋሬጣ የሚበዛባትን ጠባቧን መንገድ ምረጥ፤ በእርሷም ላይ ተጓዝ፡፡