ጾም መንፈሳዊ አዝመራ ነው፡፡ በዚህ ወቅት እንደ ወታደር ትጥቃችንን አጥብቀን፣ እንደ ገበሬ
መጭዳችንን ስለን፣ ከብኩን ዓለማዊ ከንቱ ምኞት ማዕበል ለመዳን እንደ መርከበኛ የሃሳብ ማሃልቃችንን አጥብቀን እንደ ተጓዥ
መንገዳችንን አስተካክለን ወደ መንግሥተ ሰማያት እንገስግስ፡፡ እንቅፋት፣ አባጣ ጎባጣ፣ እሾህ ጋሬጣ የሚበዛባትን ጠባቧን
መንገድ ምረጥ፤ በእርሷም ላይ ተጓዝ፡፡
እኔ የምናገረው ብዙ ሰዎች ስለሚጾሙት ጾም አይደለም፡፡ ከሥጋ ብቻ ሳይሆን ከኃጢአትም ስለሚጾምበት እውነተኛ ጾም እንጂ፡፡ ጾም ከባሕርይዋ የማይስማማ ተግበር የሚፈጽሙትን አንዳች አትጠቅምም፡፡ በጾም ደክመን የምናገኘውን ፀጋ (አክሊለ ጾም) እንዳናጣ መጠንቀቅ አለብን፡፡ ስንጾም እንዴት መጾም እንዳለብን፣ ምን ማድረግ እንደለብንና እንደሌለብን ማወቅ አለብን፡፡ ጾምማ ፈርሳውያንም ጾመዋል፡፡ በመጨረሻ ግን ባዶአቸውን ቀሩ፡፡ ከጾም ፍሬ አልተቋደሱም፡፡ ከፈሪሳዊው ጾም ይልቅ የማይጾመው ቀራጭ ትህትና በልጦ ተገኝቷል፡፡ በመልካም ምግባርና ትሩፋት ያልታጀበች ጾም ረብ ጥቅም የላትም፡፡
እኔ የምናገረው ብዙ ሰዎች ስለሚጾሙት ጾም አይደለም፡፡ ከሥጋ ብቻ ሳይሆን ከኃጢአትም ስለሚጾምበት እውነተኛ ጾም እንጂ፡፡ ጾም ከባሕርይዋ የማይስማማ ተግበር የሚፈጽሙትን አንዳች አትጠቅምም፡፡ በጾም ደክመን የምናገኘውን ፀጋ (አክሊለ ጾም) እንዳናጣ መጠንቀቅ አለብን፡፡ ስንጾም እንዴት መጾም እንዳለብን፣ ምን ማድረግ እንደለብንና እንደሌለብን ማወቅ አለብን፡፡ ጾምማ ፈርሳውያንም ጾመዋል፡፡ በመጨረሻ ግን ባዶአቸውን ቀሩ፡፡ ከጾም ፍሬ አልተቋደሱም፡፡ ከፈሪሳዊው ጾም ይልቅ የማይጾመው ቀራጭ ትህትና በልጦ ተገኝቷል፡፡ በመልካም ምግባርና ትሩፋት ያልታጀበች ጾም ረብ ጥቅም የላትም፡፡
ጾም መድኃኒት ናት፡፡ እንደ ሌሎች መድኃኒቶች ሁሉ የሚፈወስባት
አጠቃቀሙን የሚያውቅ ሰው ብቻ ነው፡፡ በአግባቡ መጠቀም የማይችል በጾም ቢጎዳ እንጂ አንዳች ጥቅም ሊያገኝ አይችልም፡፡
ጾም ዋጋ የሚያሰጠው ከምግብ በመከልከል ብቻ ሳይሆን ከኃጢአት ሥራዎችም መራቅ ነው፡፡ ሥጋ
በለመብላቱ ብቻ የጾመ የሚመስለው ቢኖር በዚህ አንዳች ነገር አያገኝም፤ ጾሙ ብላሽ ወይም ከንቱ ናት፡፡ ትጾማለህ? በሥራህ ግለጠህ
አሳየኝ፡፡ በምን ዓይነት ሥራ ይገለጣል ትለኝ እንደሆነ ለደሃ ራራለት እዘንለት፡፡ የተጣለህን ታረቀው፣ በባልጄራህ ክብር አትቅና፡፡
መልከ መልካም ሴት ስታይ ውበቷ ሳይማርክህ እለፋት፡፡ ጾም አፍህ ብቻ ሳይሆን ዐይንህ፣ ጆሮህ፣ አፍንጫህ፣ እግርህ፣ እጅ፣ በአጠቃላይ
መላ ሕዋሳትህ መጾም አለባቸው፡፡
እጆቻችን ከቅሚያና ከንፍገት በመንጻት
ይጹሙ፡፡ እግሮቻችን ወደ ሕገ ወጥ ድርጊቶችና ተግባራት ከመሮጥ ታቅበው ይጹሙ፡፡ ዐይኖቻችን ከቆነጃጅት ጋር መቦዝን ወይም ለሀይማኖት የማይመቹ
እንግዳና ማራኪ
ነገርችን ማየትን በመተው ይጹሙ፡፡ ዐይን የሚጠግበው በማየት ነው፡፡ ነገር ግን የምናያቸው ነገሮች ሕገ ወጥ፣ የተከለከሉና ለክርስትና
የማይበጁ ከሆኑ ጾማችን ይበላሻል፡፡ በአጠቃላይ ነፍሳችን ምቾትን ታጣለች፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ጥሩና መልካም ነገሮችን የምናያቸው
ከሆነ ጾማችንን እናስጌጣለን፡፡ በጾም ምክንያት ከተፈቀደልን ምግብ እንታቀባለን፡፡ በዐይናችን ግን የተከለከለውን ሁሉ እንደስሳለ፡፡
ሥጋ አልበላህም? በዐይንህ አትዳራ፤
አትሰስን፡፡ ጆሮም ይጹም፡፡ የጆሮ ጾም ክፉን አለመስማት ነው፡፡ ‹‹ሐሰተኛ ወሬ አትቀበል ሐሰተኛ ምስክርም ትሆን ዘንድ ከኃጢአተኛ
ጋር እጅህን አታንሣ›› እንዲል ዘጸ. ፳፫፥ ፩። አፍ ከአሳፋሪ ንግግሮችና ስድብ ይጹም፡፡ ወንድሞቻችንን እያማን
ከዶሮና ዐሣ ብንጾም ምን ይረባናል? ሃሜተኛ የወንድሙን ሥጋ ይበላል፤ ክፉ ተናጋሪም የባልንጄረውን አካል ይነድፋል፡፡ ስለዚህም
ቅ/ጳውሎስ እንዲህ ያስጠነቅቃል፡-ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱና ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ ገለ.
፭፥ ፲፭፡፡
በሥጋዊ ጥርስህ አልነከስከውም፤
ሥጋውንም ቦጭቀህ አልጎረስክም፡፡ ነገር ግን የሃሜት ጥርስህን ነፍሱ ላይ ተክለህ በክፉ ጥርጣሬ ቁስል አሰቃየኸው፡፡ በሃሜት ነክሰህ
አቆሰልከው፡፡ በክፋት መንፈስ ራስህንና ሌሎች ሰዎችን ጎዳህ፡፡ ባልጄራህን የስድብ ሸማ አለበስከው፡፡ በእቡይ ሥራህ ከበጎ መንገድ
አሰናክለህ ክፉ ሰውም አደረግከው፡፡ እርሱም በሕይወት ዝሎ በሌሎች ክፋት ይተባበራል፡፡ በብዙ ፈተና ይወድቃል፣ እየታበየም በሰዎች
ኃጢአት ተጠያቂ ይሆናል፡፡ አልፈህ ተርፈህ ለቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ ሕይወት ደንቃራ ትሆናለህ፡፡ ተከታዮችም በኃጢአት የተፈረጁትን
ብቻ ሳይሆን ጠቅላላ ክርስቲያኖችን ይቃወማሉ፤ ይከሳሉም፡፡
ስለዚህ በጾም ወቅት ልትተገብራቸው የሚገቡ ሦስት መመርያዎችን በአእምሮህ ውስጥ ማስቀመጥ እወዳለሁ፡- ስለማንም ክፉ አታውራ፣ ማንንም ጠላት አይሁንህ፣ ክፉ የስድብ ልማድን ከአፍህ አርቅ፡፡
ገበሬ የድካሙን ዋጋ ቀስ በቀስ እንደሚያገኝ ሁሉ እኛም እነዚህን መመርያዎች ብንከተል በሂደት ወደ ትክክለኛው የጾም
ተግበር እንደርሳለን፡፡ ከጾሙ በረከት አግኝተን በመንፈሳዊ ጥበብ እናድጋለን፡፡ በዚህም ሕይወት የተስፋ አዝመራ እናዘምራለን፡፡
በክርስቶስ ፊት በክብር ቆመን በሰው አንደበት ሊነገር የማይቻለውን የእግዚአብሔር ስጦታና በረከት እንቀበላለን፡፡ በጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ፀጋ፣ በአባቱ ክብር፣ በመንፈስ ቅዱስ ለዘለዓለም በደስታ እንኖራለን፡፡
አሜን፡፡
No comments:
Post a Comment