Thursday, March 17, 2016

መልካሙ እረኛ ክርስቶስ


መልካም እረኛ እኔ ነኝ፡፡ የእራሴ የሆኑትን አውቃቸዋለሁ፤ እወዳቸውማለሁ፤ እነርሱም ያውቁኛል፡፡ በግልጽ ቋንቋ የሚወዱኝ ይከተሉኛል፤ እውነትን የማይወድ ግን እኔን አያውቀኝም፡፡
ውድ ወንድሞቼ፡- እናንተም ፈተና እንዳለባችሁ ጌታችን እንዴት ባሉ ቃለት እንደገለጸ እዩ፡፡
እናንተ ከመንጋው መሆናችሁን፣ እርሱን አውቃችሁ የእውነት ብርሀኑ በአእምሮአችሁ ውስጥ እያበራ መሆኑን እራሳችሁን ጠይቁ፤ ሕሊናችሁን መርምሩ፡፡ እኔ በእወነት እነግራችኃለሁ፡- እርሱን ማወቅ የምትችሉ በእምነት አይደለም፡፡ ፍቅር ግን ወደ እርሱ ታደርሳችኃለች፡፡ ወደ እርሱ የሚያቀርባችሁ ባዶ እምነት ሳይሆን ሥራ ነው፡፡ ለዚህ ምስክሬ ወንጌላዊ ዮሐንስ ነው፡፡ ‹‹ትእዛዛቱን ሳይጠብቅ እግዚአብሔርን አውቀዋለሁ የሚል ሁሉ ውሸታም ነው›› ይለናል፡፡
በማስከተልም ጌታ፡- ‹‹አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ›› ብሏል። ስለበጎቼ ነፍሴን አሳልፌ እሰጣለሁ በማለት እርሱ አባቱን እንደሚያውቅ አባቱም ደግሞ እርሱን እንደሚያውቀው ግልጽ ማረጋገጫ ሰጥቶናል፡፡ በሌላ አነጋገር ለበጎቹ ያለውን ፍቅር በሞት በመገለጽ ለአባቱ ያለውን ታላቅ ፍቅር አሳየን፡፡ እንደገናም እንዲህ አለ፡- ‹‹በጎቼ ድምጼን ይሰማሉ፣ እኔም አውቃቸዋለሁ፣ እነርሱም ይከተሉኛል፣ እኔም የዘላለም ሕይወት እሰጣቸዋለሁ››፡፡ አስቀድሞም፡- ‹‹ወደ በጎቹ ጎረኖ በእኔ በኩል የሚገባ ሁሉ ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማርያም ያገኛል፣ መልካም ደስታም ይሆንለታል›› አለ። ሰው በዚህ መንገድ ወደ እምነት ሕይወት ይገባል፣ በእምነትም ራእይ ይገለጥለታል፣ በሀይማኖት ይመሰጥና በደስታ መስክ ለዘለዓለም ይሰማራል፡፡
ስለዚህ የጌታችን በጎች በመጨረሻ ሰኣት በቅን ልቡናቸው የተከተሉት ሁሉ ወደ ሚመገቡበት ዘለዓለማዊ የደስታ ለምለም መስክ ይሰማራሉ፡፡ ይህም ሰማያዊ ደስታ ነው፡፡ በዚያም የተመረጡት የእግዚአብሔርን ፊት በደስታ ያያሉ፡፡ ለዘመናት በታላቅ በዓል ዘለዓለማዊ የሕይወት ግብዣ ይደረግላቸዋል፡፡ እንግዲህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ ይህን ሰማያዊ አስደሳች በዓል ከአእላፍ መንፈሳያውን ዜጎቻችን ጋር ለማክበር እንዘጋጅ፡፡ የደስታ ምንጭ ቅን ሃሳባቸው በእኛ ላይ ትደር፡፡ ልባችን በሰማይ ይሁን፣ እምነታችን ይብራ፣ የተዘጋጀችልንን መንግሥተ ሰማያት ተስፋ እናድርግ፡፡ እርስ በርስ መፈቃር ሰማያዊ መንገድ ነው፡፡
ምንም ዓይነት ፈተና ቢያጋጥመን ከሰማያዊ ደስታ እንዲያደናቅፈን መፍቀድ የለብንም፡፡ የመንዱ አባጣ ጎባጣነት ማንንም ከጉዞው ሊያሰናክለው አይገባም፡፡ ስኬትና ውበት ያማልሉን ዘንድ መፍቀድ የለብንም፡፡ ወይም በሚያልፍበት መንገድ ላይ ያለው የመስኩ ውበትና ልምላሜ የት እንደሚሄድ አስረስቶ ከጉዞው ያስተጓጎለው ሰነፍ መንገደኛ መምሰል የለብንም፡፡   
ታላቁ ጎርጎርዎስ  

No comments:

Post a Comment