በወዳጁ በነቢዩ ዮናስ ስብከት የሕዝበ
ነነዌን እዝነ ልቡና ከፍቶ በንሥኃ ወደ ራሱ የጠራ፤ ምህላ ጸሎታቸውን ተቀብሎ ቁጣውን በምህረት፣ መዓቱን በትእግስት የመለሰ አምላክ፤
ዛሬም በጾመ ነነዌ ፍጻሜ በቸሪት እናቱ ሰዓሊተ ምህረት፣ አቁራሪተ መዓት፣ አፍጣኒተ ረድኤት፣ ምዕረገ ጸሎት፤ በእለተ ኪዳነ ምሕረት
እክለ በረከቱን ሊመግበን ዝናመ ምሕረቱን አውርዶልናል፡፡
Thursday, February 25, 2016
Wednesday, February 24, 2016
ኪዳነ ምሕረት
ዲ/ን ኅብረት የሺጥላ
'ኪዳን'
የሚባለው ቃል "ቃል" ከሚለው ጋር እየተቀናጀ በብሉይ ኪዳን ለ280 ጊዜ ያህል ሲጠቀስ በአዲስ ኪዳን ደግሞ ከ33 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፡፡ "ኪዳን" ቃሉ "ተካየደ" ተማማለ፣ ቃል ተገባባ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡
"ምሕረት"
የሚለው ቃል ደግሞ ማብራሪያ ሳያሻው ምሥጢሩ ከነዘይቤው ከግእዝ የተወረሰ ነው፡፡ ስለዚህ ኪዳነ ምሕረት ማለት የምሕረት፣ የይቅርታ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ ኪዳን ከተራ ውሎችና ስምምነቶች የበለጠ ጽኑና ቀዋሚ ነው፡፡ ከፍ ያለ ክብደትም አለው፡፡
|
Monday, February 22, 2016
ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፡፡ ዮናስ ፩፥ ፪ ክፍል ፩
ይህ ከእግዚአብሔር ለሰው ልጅ የተሰጠ ትእዛዝ ነው፡፡ ለነቢዩ ዮናስ የተሰጠ የሕይወት አድን መመርያ፣ ሰውን የማዳን ተልእኮ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ዓላማ ሰውን ማዳን ነው፡፡ ዮናስ ማለት ርግብ፣ የዋህ ማለት ነው፡፡ ዮናስ የዋህ ነቢይ ነው፡፡
ነነዌ ከአንድ መቶ ሃያ ሺ በላይ
ሕዝብ የሚኖርባት ታላቅ ከተማ ናት፡፡ ነነዌ በነቢያት ብዙ ሸክም (ኃጢአት) የተነገረባት፣ የእግዚአብሔር ቁጣ የተቃጣባት የኃጢአት
አምባ ናት፡፡
Friday, February 19, 2016
ለክርስቲያን መከራ ጌጡ እሳት ሽልማቱ ነው፡፡
አባቶቻችን አብያተ ክርስቲያናትን አንጸው ታቦት አስቀርጸው ኢትዮጵያ ሀገራችን በረከተ እግዚአብሔር እንድታገኝ አድርገው ለዓለም ሰላም ሲጸልዩ ኖረዋል፡፡ አሁን አሁን ግን የእሳት ልጅ አመድ እንዲሉ ለሀገር ፍቅር ለወገን ክብር የሌላቸው፣ ሰላም የራቃቸው፣ ፍጹም ኢትዮጵያዊነት የማይሰማቸው፣ በሴይጣናዊ አስተሳሰብ የተቃኙ ታሪክ በራዥ ቅርስ አጥፊዎች አብያተ ክርስቲያናትን ማቃጠል ጀምረዋል፡፡ ድንቁርናቸው ነው እንጂ እነዚህ ወገኖች የሚጎዱት ክርስቲያኖችን ሳይሆን ራሳቸውን ነው፡፡ የሚያፈርሱት የእግዚአብሔርን ቤት ሳይሆን ሀገርን ነው፡፡ አይ አለማወቅ! ለክርስቲያን እኮ እሳት ብርቁ አይደለም፡፡ መከራ ጌጡ፣ እሳት ሽልማቱ፣ ስደት ሕይወቱ ነው፡፡
Tuesday, February 16, 2016
Subscribe to:
Posts (Atom)