አባቶቻችን አብያተ ክርስቲያናትን አንጸው ታቦት አስቀርጸው ኢትዮጵያ ሀገራችን በረከተ እግዚአብሔር እንድታገኝ አድርገው ለዓለም ሰላም ሲጸልዩ ኖረዋል፡፡ አሁን አሁን ግን የእሳት ልጅ አመድ እንዲሉ ለሀገር ፍቅር ለወገን ክብር የሌላቸው፣ ሰላም የራቃቸው፣ ፍጹም ኢትዮጵያዊነት የማይሰማቸው፣ በሴይጣናዊ አስተሳሰብ የተቃኙ ታሪክ በራዥ ቅርስ አጥፊዎች አብያተ ክርስቲያናትን ማቃጠል ጀምረዋል፡፡ ድንቁርናቸው ነው እንጂ እነዚህ ወገኖች የሚጎዱት ክርስቲያኖችን ሳይሆን ራሳቸውን ነው፡፡ የሚያፈርሱት የእግዚአብሔርን ቤት ሳይሆን ሀገርን ነው፡፡ አይ አለማወቅ! ለክርስቲያን እኮ እሳት ብርቁ አይደለም፡፡ መከራ ጌጡ፣ እሳት ሽልማቱ፣ ስደት ሕይወቱ ነው፡፡
የተከበራችሁ የማኅቶት ታዳሚያን በአንዳንድ ማሕበራዊ ድረ ገጾችና ዜና ማሰራጫዎች በኦሮምያ ክልል ምእራብ አርሲ ዞን በርካታ አብያተ ክርስቲያናት መቃጠላቸውን ሰምቼ አንድ የመጽናኛ መልእክት ለክርስቲያኖች ለማስተላለፍ ስነሳ ፌስ ቡክ ላይ ተለጥፏ ያገኘኸትን ጥሩ መልእክት የሰነቀች ጽሑፍ ተጋርቻታለሁና እንደሚከተለው ያንብቡአት፡፡
ክርስትናን እሳት የሚያሸንፈው ቢሆን ኖሮ ድምጥያኖስና ዲዮቅልጥያኖስ በተሳካላቸው ነበር፡፡ ክርስትናን መግደል የሚያሸንፈው ቢሆን
ኖሮ አይሁድና ሮማውያን፣ ኮሙኒስቶችና ማኦኢስቶች ድል በነሡት ነበር፡፡ ክርስትና በቤተ ክርስቲያኖች
መቃጠል፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም መቆነጻጸል የሚያበቃለት ቢሆን ኖሮ ኔሮንና ትራጃን፤ ዮዲት ጉዲትና ግራኝ ባስቆሙት ነበር፡፡ ክርስትና እሳት ሆኖ በእሳት ውስጥ ማለፍ ነው፡፡ ክርስትና እሳትን እሳት ሆኖ ድል መንሣት ነው፡፡ እዚህ እሳት ላይ ሦስቱ ሕጻናት ተጥለው ነበር፣ እዚህ እሳት ውስጥ ቂርቆስና እየሉጣ ተወርውረው ነበር፡፡ ይኼ እሳት ቅዱስ ፖሊካርፐስን በልቶት ነበር፡፡ ክርስትና ግን ይኼው አለ፡፡ ሊያጠፉት የተነሡት ሁሉ ተረት ሆነዋል፡፡ ክርስትና ግን ህያው ሆኖ አለ፡፡ የሠራነውን ቤተ ክርስቲያን ያቃጥሉ ይሆናል፣ የሠራነውን ሰማያዊ ቤት ግን አይደርሱበትም፡፡ ንብረታችንን ይወስዳሉ፣ እምነታችንን አያገኙትም፤ እኛን ይገድላሉ፤ ነፍሳችን ግን ከዐቅማቸው በላይ ናት፡፡ ይህንን መከራ አስቀድመን የማናውቀው ቢሆን ኖሮ በደነገጥን ነበር፡፡ ነገር ግን ክርስቲያን ስንሆን ይህ እንደሚመጣ እናውቅ ነበር፡፡ ‹ተዘጋጅታችሁ ተቀመጡ› ተብለናልና ተዘጋጅተን ነበር፡፡ እኛ ቆንጨራና ቦንብ፣ መትረዪስና አዳፍኔ አንይዝም፡፡ እኛ በጠጠር ጎልያድን የሚረታውን ይዘናል፡፡ በጩኸት ሳይሆን በዝምታ ኢያሪኮን የሚንደውን ይዘናል፡፡ በሁካታ ሳይሆን በእርጋታ የሚሠራውን ይዘናል፡፡ እነርሱ ሲጮኹ ከአጋንንት ጋር ያውካሉ፤ እኛ ግን ዝም ስንል ከፈጣሪያችን ጋር እንነጋገራልን፡፡ ዛሬ በምድር ላይ የለኮሱትን እሳት ብዙዎች በሰማይ እነርሱው ይቀበሉታል፡፡ አይቀርም፤ አምላካችንም ዝም አይልም፡፡ እንገደላለን፤ ግን እናሸንፋለን፤ እንቃጠላለን፤ ግን እንለመልማለን፡፡ እናጣለን፤ ግን እናገኛለን፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከተቃጠሉት ሕንጻዎቿ በላይ ናትና፡፡ የቅዱሳን አምላክ ከተዋህዶ በረት አያናውጸን፣ አምነው ነበር ካዱ፣ ተሰብስበው ነበር ተበተኑ ከመባል እመብርሀን የሁላችንንም ፍጻሜ ታሳምርልን፣ የሰማዕታቱ ምልጃና ጸሎት አይለየን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይቆየን፡፡
No comments:
Post a Comment