ክፍል ሁለት
ከዚህ
ሁሉ ባሻገር እሰድራኤላውያኑ ሌሎች ብዙ ማህበራዊና መንፈሳዊ የሆኑ ከባድ ሸክሞች ነበሩባቸው፡፡የሮማውያንን የቅኝ ግዛት ቀንበር
አሽቀንጥረው ለመጣል የተደራጁ አደጋ ጣይ ብዙ የነፃ አውጪ ግንባሮች፤በአንጻሩ ደግሞ እንደ ፈሪሳውያን፣ሰዱቃውያን፣ኤሴውያን
የመሳሰሉ ሃይማኖታዊ ካባ ለባሽ ቡድኖች ነበሩ፡፡Sunday, March 29, 2015
Friday, March 27, 2015
፯. ኒቆዲሞስ
ሰባተኛው እሑድ ኒቆዲሞስ ይባላል፡፡
በሌሊት ወደ ጌታ መጥቶ ይማር የነበረው የኒቆዲሞስን ታሪክ የሚያወሳ ስብከት ይሰበካል፤ መዝሙር ይዘመራል፡፡
ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊና የአይሁድ አለቃ
ነው፡፡ ፈርሳውያን የጌታ ተቀዋሚዎች ናቸው፡፡ ኒቆዲሞስ በዘመኑ ከነበሩት ተላላቅ የአይሁድ ምሑራን አንዱ ነበር፡፡ ኒቆዲሞስ የሕግ
አዋቂ፤ የሕግ ምሑር ነው፡፡
Monday, March 23, 2015
ሸክማችሁ የከበደ ደካሞች ሁሉ ወደ እኔ ኑ፡፡ ማቴ.፲፩÷፳፰
ክፍል አንድ
የትምህርቱ ዓላማ ፡-ድካማችንን ተገንዝበን ከድካማችን ሁሉ ወደሚያሰርፈን አምላክ
እንድንቀርብ የንስሓ ጥሪን ማስተጋባት ነው፡፡
ሸክም የሚከብድ፣የሚያደክም፣የሚያሳስብ ከባድ ነገር ሲሆን፤የሸክም ምሥጢራዊ ትርጉሙ ደገሞ ሓጢአት፣መከራ፣በሽታ፣ችግር፣አደራ፣ሀላፊነትየመሳሰሉትን
ያመለክታል፡፡በዚህ ትምህርታችን የምንማረው ስለአንድ ከባድ ቁስ ሳይሆን በዚህ በሸክም ምሥጢራዊ ትርጉም ላይ ተመርኩዘን ጌታ ኢየሱስ
ክርስቶስ ያስተማረውን ትምህርት በአጭሩ እንመለከታለን፡፡
Friday, March 20, 2015
፮. ገብር ሔር
ስድስተኛው እሑድ ገብር ሔር ይባላል፡፡
ገብር ሔር ማለት መልከም ባርያ ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ በዚህ ሳምንት የተጣለባቸውን አደራ ተቀብለው በታማኝነት ኃለፊነታቸውን
የተወጡ መልካም አገልጋዮች በጌታቸው ፊት መወደሳቸውና መሸለማቸው ይወሳል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ የተሰጠውን አደራ ቸል ብሎ ኃላፊነቱን
ያልተወጣ እኩይ ሎሌ በጌታው መወቀሱና መቀጣቱ የሚነገርበት የሚወሳበት ሳምንት ነው፡፡
ይህ ታሪክ በማቴዎስ ወንጌል በሰፊው
ተብራርቶ ተነግሯል፡፡ አስመ ከመ ብእሲ ዘይነግድ ወጸውኣ አግብርቲሁ ወወሀቦሙ ንዋዮ ይትገብሩ ቦቱ …፡፡ ማቴ. ፳፭ ÷ ፲፬ -
፴ ፡፡ |
Saturday, March 14, 2015
፭. ደብረ ዘይት
አምስተኛው እሑድ ደብረ ዘይት ይባላል፡፡ ደብረ ዘይት ማለት የወይራ ተራራ
ማለት ነው፡፡ ደብረ ዘይት ብዙ የወይራ ዛፍ ያለበት ተራራ ሲሆን ስያሜውንም ያገኘው ከዚሁ ነው፡፡ ጌታ በደብረ ዘይት ተራራ ተቀምጦ
ስለዳግም ምጽዓት ወይም የዓለም መጨረሻ ለቅዱሳን ሓዋርያቱ አስተምሯል፡፡ ጌታችን ቅዱሳን ሐዋርያቱን አስከትሎ ከመቅደስ ወጥቶ ወደ
ደብረ ዘይት ተራራ ሲሄደ ሐዋርያት የሰሎሞንን ቤተ መቅደስ ውበት የድንጋዩን አጠራረብ፣ ንድፈ ሕንፃውን፣ የወርቅ ዝምዝሙን፣ የሓር
ጭምጭማቱን አይተው ተደነቁ፡፡ ግታም መልሶ፡- ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ
አይቀርም አላቸው። ይህን ውብ ሕንፃ የነደፉ እጆች በሞት ይታሰራሉ፣ ይሁን ድንቅ ንድፍ ያፈለቀ አእምሮ ይያዛል፤ በድንጋይ የተመሰለ
ሕንፃ ሰውነታችሁ ይፈርሳ፣ በሞት ይለወጣል፡፡ ይህች በጨረቃ ደምቃ፣ በከዋክብት አሸብርቃ፣ በፀሓይ ሙቃ በውበቷ ምታማልላቸው ዓለም
ታልፋለች አላቸው፡፡
Friday, March 6, 2015
፬. መጻጉዕ
አልጋህን ተሸክመህ ሂድ፡:
አራተኛው እሁድ መጻጉዕ ይባላል፡፡ መጻጉዕ ማለት በሽተኛ ማለት ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕበራይስጥ ቤተ ሳይዳ ወደምትባል አንዲት መጠመቂያ ወርዶ በልዩልዩ ደዌያት የተያዙ ብዙ ሕሙማንን መፈወሱ የሚወሳበት፣ የሚዘመርበት ሳምንት ነው፡፡ በተለይም ለሰላሳ ስምንት ዓመታት በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ ተይዞ የነበረው አንድ ሕሙም በጌታ ቃል ተፈውሶ አልጋውን ተሸክሞ ወደ ቤቱ መሄዱ በቅዱስ መጽሓፍ በጉልህ ተመዝግቧል፡፡
Sunday, March 1, 2015
፫. ምኩራብ
|
Subscribe to:
Posts (Atom)