ሶስተኛው እሁድ ምኩራብ
ነው ፡፡ በዚህች ሰንበት ጌታ ወደ ምሁራብ ገብቶ ማስተማሩ ይነገራል ፤ ይወሳል ፡፡ ወደ ቅፍረናሆምም ገቡ ፤ ወዲያውም በሰንበት
ወደ ምኩራብ ገብቶ አስተማረ ፡፡ ማር .፩ ፥ ፳፰፡፡
|
|
ምኩራብ የኤሁድ ቤተ ጸሎት ናት
፡፡ በአይሁድ ሕግ ከኢየሩሳሌም ውጭ ቤተ መቅደስ መሥራት አይፈቀድም ፡፡ ምክንያቱም ቤተ መቅደስ የታቦተ ጽዮን መኖሪያ ስለሆነች
፡፡ ታቦተ ጽዮን የነበረችው ደግሞ ኢየሩሳሌም ነበር ፡፡ ከኢየሩሳሌም ውጭ የነበሩ ቤተ አይሁድ በያሉበት ቦታ ምኩራብ ሠርተው ይጸልዩባት
፤ ትንቢተ ነቢያትን ፤ ሕግጋተ ሙሴን ይማሩባት ነበር ፡፡ በአንፊጶልና በአጶሎንም ካለፉ በኋላ ወደ ተሰሎንቄ መጡ ፤ በዚያም የአይሁድ
ምኩራብ ነበረ ፡፡ የሐዋ. ፲፯ ፥ ፩ ፡፡ እነዚህ ከኢየሩሳሌም ውጭ የነበሩ ቤተ አይሁድ በዐመት አንድ ጊዜ ለክብረ በዓል ወደ
ኢየሩሳሌም ይሄዱ ነበር ፡፡ የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ በሆነ ጊዜ እንደ በዓሉ ሥርዓት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ ፡፡ ሉቃ. ፪ ፥ ፵፪
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
በዚህች ሰንበት ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ሥጋውያን ነጋዴዎችንና ሥጋዊ ንግድን በጅራፍ ገርፎ ከቤተ መቅደስ አስወግዷል ፡፡ ጅራፍ በቤተ እግዚአብሔር ያልተገባ ሥጋዊ ተግባር
በሚፈጽሙ ሥጋውያን ላይ የሚታዘዝ የእግዚአብሔር መቅሰፍት ነው ፡፡ የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር ፣ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ
፡፡ በመቅደስም በሬዎችንና በጎችን ፤ ርግቦችንም የሚሸጡትን ፣ ገንዘብ
ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ ፤ የገመድ ጅራፍም አበጅቶ ፤ ሁሉን በጎችንም ፣ በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው ፤ የለዋጮችንም ገንዘብ
አፈሰሰ ፣ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፣ ርግብ ሸጮችንም፡- ይህን ከዚህ ውሰዱ ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው ፡፡
ዮሐ. ፪ ፥ ፲፫ - ፲፮፡፡
ዛሬም ቤተ ክርስቲያን ብዙ ሥጋውያን
ነጋዴዎች መናኸርያ ፣ የአስመሳይ ወንበዴዎች ዋሻ ሆናለች ፡፡ የቤተ ክርስቲያን ልጆች መስለው የቤተ ክርስቲያን ልጆች ያልሆኑ ፤
የእግዚአብሔር መስለው የእግዚአብሔር ወገን ያልሆኑ የበግ ለምድ የለበሱ ብዙ ነጋዴዎች ለሥጋዊ ፍላጎታቸው ስኬት በቤተ ክርስቲያን
መሽገዋል ፡፡
የአስመሳዮች ትልቋ የሥጋ ገበያ
ማዕከል ቤተ ክርስቲያን ሆናለች ፡፡ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን እንገነባለን ብለው የራሰቸውን ቤት የሚገነቡ ፣ በልማት ኮሚቴ ስም የራሳቸውን
ኪስ የሚያደልቡ ፣ በመንፈሳዊ ጉዞ ስም የሚነግዱ በግ መሳይ ብዙ ነጣቂ ተኩላዎች አሉ ፡፡ አሁን አሁንማ ካህኑ የሚቀድሰው ፣ ዘማሪው
የሚዘምረው ለእግዚአብሔር ሳይሆን ለብር ሆኗል ፡፡ ሰባኪው የሚሰብከው ሰውን ለማዳን ሳይሆን ዝናውን ነኝቶ ሀብት ለማካበት ነው ፡፡
ወገኖቼ ክርስቲያኖች ክርስቶስ የቁጣ
ጅራፍ ይዞ ሳይመጣ በቤተ ክርስቲያን የምናከሄደውን ሥጋዊ ንግድ ሁሉ በንሥሐ አስወግደን ክርስቲያናዊ ተግባራትን እንፈጽም ፡፡
የእለቱ መዝሙር ፡- ቦዐ ኢየሱስ
ምኩራበ አይሁድ
ምንባብ ፡- ቆላ. ፪ ፥ ፲፮ -
፳፫ ፤ ያዕ. ፪ ፥ ፲፲፰ - ፳፩ ፤ የሐዋ. ፭ ፥ ፲፯ - ፳፩
ምስባክ ፡- እስመ ቅንዓተ ቤትከ
በልዓኒ ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዓየሩከ ወድቀ ላእለየ ወቀጻዕክዋ በፆም ለነፍስየ ፡፡ መዝ. ፷፰(፷፱) ፥ ፱ -፲
ወንጌል ፡- ዮሐ. ፪ ፥ ፲፪ - ፳ |
No comments:
Post a Comment