ሁለተኛው እሁድ ቅድስት ይባላል ፡፡ በተለይ ስለ እለተ ሰንበት ቅድስና ስለሚያወሳ ቅድስት ተብሏል ፡፡ እለተ ሰንበት እለት ዕረፍት እለት ቅድስት ናት ፡፡ በመዝገበ ፍጥረት መጽሐፍ እንደተገለፀው አምላክ ገቢረ ፍጥረታትን አጠናቅቆ አርፎበታል ፡፡ ሰማይና ምድር ሠራዊቶቻቸውም ሁሉ ተፈፀሙ ፡፡ እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ ፤ በሰባተኛውም ቀን ከሥራው ሥራ ዐረፈ ፡፡ እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም ፤ እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና ፡፡ ዘፍ. ፪ ፥ ፩ - ፫ ፡፡
Saturday, February 21, 2015
፪. ቅድስት
ሁለተኛው እሁድ ቅድስት ይባላል ፡፡ በተለይ ስለ እለተ ሰንበት ቅድስና ስለሚያወሳ ቅድስት ተብሏል ፡፡ እለተ ሰንበት እለት ዕረፍት እለት ቅድስት ናት ፡፡ በመዝገበ ፍጥረት መጽሐፍ እንደተገለፀው አምላክ ገቢረ ፍጥረታትን አጠናቅቆ አርፎበታል ፡፡ ሰማይና ምድር ሠራዊቶቻቸውም ሁሉ ተፈፀሙ ፡፡ እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ ፤ በሰባተኛውም ቀን ከሥራው ሥራ ዐረፈ ፡፡ እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም ፤ እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና ፡፡ ዘፍ. ፪ ፥ ፩ - ፫ ፡፡
Wednesday, February 18, 2015
ኢየሩሳሌም
ክፍል አንድ
ኢየሩሳሌም ፡- የሰላም ፣ የፍቅ፣ የደስታ ከተማ ብትባልም
፩. ዘወረደ
አንደኛው እሑድ ዘወረደ ይባላል፡፡ኃያል አምላክ የሰው ፍቅር አገብሮት
ከሰማየ ሰማያት መውረዱ ፤ ሰው ሆኖ መወለዱ ፤ መሰቀሉ የሚወሳበት ሳምንት ነው ፡፡ ከፈጣሪው ተጣልቶ የነበረ አዳም መታረቁ የሚነገርበት
በመሆኑ ዘወረደ ስብከተ ተፋቅሮ ነው ፡፡
Monday, February 16, 2015
ጾም
ጾም (ጦም) ማለት ለተወሰነ ጊዜ እህል ከመብላት ውሃ ከመጠጣት መታቀብ ወይም ለተወሰኑ ወራት ከጥሉላት ምግቦች መከልከል ማለት ነው ፡፡ የጾም ሀይማኖታዊ ትርጉም ሰውነት ከሚያስፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ መከልከል ፤ መወሰን ፤ ለሰውነት የሚያጎመዠውን ነገር ሁሉ መተው ፤ ለሰው ሁሉ መልካሙንና በጎውን ማድረግ ፤ ሰውንም ሆነ እግዚአብሔርን ከሚያሳዝን ክፉ ሁሉ መራቅ ነው ፡፡ ጾም ፈጣሪን መለመኛ ከሐጢአት ቁራኝነት መላቀቂያ መሣሪያ ስለሆነ በጾም ወራት ሕዋሳት ሁሉ ከክፉ ሥራ መቆጠብ አለባቸው ፡፡ ይጹም ዓይን ፤ ይጹም ልሳን ፤ እዝንኒ ይጹም እምሰሚዓ ሕሱም በተፋቅሮ [1]፡፡ አንድ ክርስቲያን በጾም ወራት ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ጊዜ ሕዋሳቱን ሰውንና እግዚአብሔርን ከሚያሳዝኑ ክፉ ሓሳቦችና ተግባራት መቆጠብና መከልከል አለበት ፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)