Wednesday, February 18, 2015

ኢየሩሳሌም

ክፍል አንድ 
ኢየሩሳሌም ፡- የሰላም ፣ የፍቅ፣ የደስታ ከተማ ብትባልም
ሌላ ደግሞ በጎ ያልሆነ ገጽታ አላት[1] ፡፡ ኢየሩሳሌም የመዳን ቀኗን ያላወቀች ፤ ከበረከተ ድኅነቱ ማዕድ ያልተቋደሰች ፤ ከፍቅር ጽዋ ያልተጎነጨች ፤ ደስታዋን የገፋች ፤ ከሰላም ጉባኤ ያልዋለች ፤ የመድኃኒቷንም የሕይወት ጥሪ ያልሰማች ፤ ጌታ ያለቀሰላት አሳዛኝ ከተማ ናት ፡፡ኢየሩሳሌም  ኢየሩሳሌም እንተ ትቀትሎሙ ለነቢያት ወእንተ ትዌግሮሙ  ለሐዋርያት ለእለ ተፈነው ኀቤሃ ሚመጠነ ፈቀድኩ አስተጋብኦሙ ለውሉድኪ ከመ እንተ ታስተጋብእ ዶርሆ አፍርኀቲሃ ታሕተ ክነፊሃ ወአበይክሙ ፡፡ ናሁ ይትኀደግ ለክሙ ቤትኪሙ  በድወ ፡፡ አማን እብለክሙ ኢትሬእዩኒ እምይእዜ እስከ ሶበ ትብሉ ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔ ር ፡፡ ኢየሩሳሌም  ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ነቢያትን የምትገድል ወደእርሷ የተላኩትንም የምትወግር፣ ዶሮ ጫቹቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድኩ! አልወደዳችሁምም ፡፡ እነሆ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል ፡፡ እላችኋለሁና በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም ፡፡ ማቴ. ኧ፫ ፥ ፴፯ - ፴፱ ፡፡

No comments:

Post a Comment