Sunday, September 11, 2016
Friday, September 9, 2016
ወርኃ ጳጉሜ
እንኳን ለወርኃ ጳጉሜ በሰላም አደረሰን
የዘመናት ጌታ ቸሩ አምላካችን ቀሪውን ተረፈ ዘመን በሰላም አስፈጽሞ ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ ያሸጋግረን ፡፡ አሜን ፡፡
ውድ የማኅቶት ዘተዋሕዶ እድምተኞች እንደምን ከረማችሁ ?
ከዚህ በመቀጠል ውሉደ ተዋሕዶ ለፌስ ቡክ ገጼ ላይጳጉሜ ምን ማለት ነው ? ለምንስ አምስትና ስድስት ቀን ሆነች ? ብለው ለጠየቁኝ ጥያቄ አጠር ያለች መልስ እሰጣለሁ ተከታተሉኝ ፡፡ መልካም ንባብ ፡፡
ጳጉሜ ማለት ተረፍ ማለት ነው ፡፡ ከአስራ ሁለቱ የዓመቱ ወራት በዘመን ውስጥ የተረፈች ፣ የቀረች ተረፈ ዘመን ናት ፡፡ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር አንድ ዓመት 365 ቀናት ፣ 6 ሰዓታትና 15 ኬክሮስ ነው ፡፡ ይህም ማለት አንድ ዓመት እያንዳንዳቸው ሣላሰ ሣላሳ ቀናት ያላቸው አስራ ሁለት ወራትና (ከመስከረም እስከ ነሓሴ) አምስት ቀናት ከስድስት ሰዓታት ያሉኣት አስራ ሦስተኛ ወር ወርኃ ጳጉሜ አሉት ፡፡ በዚህ መሠረት ጳጉሜ ወትሮ አምስት ቀን ከስድት ሰዓት ስትሆን በአራት ዓመት አንዴ (በዘመነ ዮሓንስ) ሽርፍራፊዎቹ ሰዓታት ተደማምረው አንድ ቀን ይሞላሉ ፡፡ በዚህ ጊዜ ጳጉሜ ስድስት ቀን ትሆናለች ፡፡
ለፍጡር ሁሉ ልኬትና ስፍር አለው ፡፡ እንደዚሁ ሁሉ ለዘመንም ልኬት ፣ ስፍርና ቁጥር አለው ፡፡ ዘመን በቁጥር ይሰላል ፤ በሰዓታት ፣ በእለታትና በአዝማናት ተሰልቶ ይቀመራል ፡፡ በዚህ በዘመን ስሌት ቀመር ወርኃ ጳጉሜ አመስት ቀናት ስትሆን በዘመነ ዮሓንስ ስድስት ቀን ትሆናለች ፡፡ የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብርቅየ ሀብት ነው ፡፡
ከዚህ በተረፈ ሰፊውን ትንታኔ ለስነ ፈለካት የቤተ ክርስቲያን ሙሑራን ትቻለሁ ፡፡
ውድ ጠያቂዎቼ፡ ለጠቅላላ ግንዘቤ ይህችን ያህል ካልኩአችሁ አበው ሊቃውንት አስፍተው ፣ አራቀው ፣ አመስጥረውና ተርጉመው እንዲያስረዱችሁ ወደ ቤተ ክርስቲያን ጎራ በሉ የማኅቶት መልእክት ነው ፡፡
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን ፡፡
Thursday, August 11, 2016
እንደ ሶስት ሰው ሆኜ ነው የምኖረዉ፡፡
"እንደኔ እንደኔ የዚህ ሀገር ችግር ከፖለቲከኞቹ በላይ ሃይማኖቶቹ መሪዎች ናቸው ብዬ አስባለሁ"
(መጋቢ ሀዲስ እሸቱ)
እዚህ ሀገር ላይ ስኖር እንደ ሶስት ሰው ሆኜ ነው የምኖረው፡፡
(መጋቢ ሀዲስ እሸቱ)
እዚህ ሀገር ላይ ስኖር እንደ ሶስት ሰው ሆኜ ነው የምኖረው፡፡
Wednesday, June 8, 2016
የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈሰ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::
ሰኔ ፩ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ በዓመት ሁለት ጊዜያት እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ ፭ ቍጥር ፻፷፬ በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የዘንድሮዉን መደበኛ የርክበ ካህናት ስብሰባ የጉባኤው መክፈቻ ሥርዓተ ጸሎት ከተፈጸመበት ከበዓሉ ዋዜማ ከግንቦት ፲፮ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ ፩ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም ድረ ለዐሥራ ስድስት ቀናት ያህል ባደረገው ጉባኤ ጠቀሜታ ባላቸው የአጀንዳ ነጥቦች ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
Wednesday, May 18, 2016
፳፬ ሰዓት የቴሌቪዥን ስርጭት
የቤተ ክርስቲያናችን የ፳፬ ሰዓት የቴሌቪዥን አገልግሎት ከቀናት በኋላ የሙከራ ስርጭት ይጀምራል
በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በተወሰነው መሠረት፤ ቤተ ክርስቲያናችን፣ በሀገር ውስጥ እና በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ምእመናን ድምፅዋን የምታሰማበት እና መረጃ የምትሰጥበት የ24
ሰዓት የቴሌቪዥን አገልግሎት ከኹለት ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የሙከራ ስርጭቱን እንደሚጀመር ተገለጸ፡፡
የስርጭት አገልግሎቱን ለመስጠት ለወድድር ከቀረቡት ሦስት ኩባንያዎች መካከል በጠቅላይ ጽ/ቤቱ የብዙኃን መገናኛ ድርጅት ቦርድ ከተመረጠውና በእስራኤል ከሚገኘው የኮሚዩኒኬሽን ኩባንያ ጋር የሥርጭት ስምምነት ውሉ ፓትርያርኩ ኢየሩሳሌምን እየጎበኙ በነበሩበት በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ መፈጸሙም ታውቋል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)
