Thursday, March 17, 2016

መልካሙ እረኛ ክርስቶስ


መልካም እረኛ እኔ ነኝ፡፡ የእራሴ የሆኑትን አውቃቸዋለሁ፤ እወዳቸውማለሁ፤ እነርሱም ያውቁኛል፡፡ በግልጽ ቋንቋ የሚወዱኝ ይከተሉኛል፤ እውነትን የማይወድ ግን እኔን አያውቀኝም፡፡
ውድ ወንድሞቼ፡- እናንተም ፈተና እንዳለባችሁ ጌታችን እንዴት ባሉ ቃለት እንደገለጸ እዩ፡፡

Wednesday, March 16, 2016

የተሳትፎ ጥያቄ


እርስዎም ይሳተፉ፡

እውቀት የማይዘረፍ የማይመዘበር ቋሚ ሀብት ነው፡፡
ሀ. ለመሆኑ እርስዎ ስለእውቀት ምን ያህል ያውቃሉ?
ለ. እውቀት ስንት ደረጃዎች አሉአት? በመንፈሳዊ እይታ ይዘርዝሩ፡፡

Tuesday, March 8, 2016

ጾም መድኃኒት ናት (በቅ/ዮሐንስ አፈወር)

ጾም መንፈሳዊ አዝመራ ነው፡፡ በዚህ ወቅት እንደ ወታደር ትጥቃችንን አጥብቀን፣ እንደ ገበሬ መጭዳችንን ስለን፣ ከብኩን ዓለማዊ ከንቱ ምኞት ማዕበል ለመዳን እንደ መርከበኛ የሃሳብ ማሃልቃችንን አጥብቀን እንደ ተጓዥ መንገዳችንን አስተካክለን ወደ መንግሥተ ሰማያት እንገስግስ፡፡ እንቅፋት፣ አባጣ ጎባጣ፣ እሾህ ጋሬጣ የሚበዛባትን ጠባቧን መንገድ ምረጥ፤ በእርሷም ላይ ተጓዝ፡፡

Monday, March 7, 2016

የጾም ዋጋ



ጾም ዋጋ የሚያሰጠው ከምግብ በመከልከል ብቻ ሳይሆን ከኃጢአት ሥራዎችም መራቅ ነው፡፡ ሥጋ በለመብላቱ ብቻ የጾመ የሚመስለው ቢኖር በዚህ አንዳች ነገር አያገኝም፤ ጾሙ ብላሽ ወይም ከንቱ ናት፡፡ ትጾማለህ? በሥራህ ግለጠህ አሳየኝ፡፡ በምን ዓይነት ሥራ ይገለጣል ትለኝ እንደሆነ ለደሃ ራራለት እዘንለት፡፡ የተጣለህን ታረቀው፣ በባልጄራህ ክብር አትቅና፡፡ መልከ መልካም ሴት ስታይ ውበቷ ሳይማርክህ እለፋት፡፡ ጾም አፍህ ብቻ ሳይሆን ዐይንህ፣ ጆሮህ፣ አፍንጫህ፣ እግርህ፣ እጅ፣ በአጠቃላይ መላ ሕዋሳትህ መጾም አለባቸው፡፡

Friday, March 4, 2016

ዋ!... ያቺ አድዋ

ዋ!... ያቺ አድዋ
ዋ!...
አድዋ ሩቅዋ
የዓለት ምሰሶ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
አድዋ…
ባንቺ ህልውና
በትዝታሽ ብጽዕና
በመሥዋዕት ክንድሽ ዜና
አበው ታደሙ እንደገና…
ዋ!
አድዋ የዘር ዐፅመ ርስትዋ
የደም ትቢያ መቀነትዋ
በሞት ከባርነት ሥርየት
በደም ለነፃነት ስለት
አበው የተሰዉብሽ ለት፤
አድዋ
የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ
የኢትዮጵያነት ምስክርዋ
አድዋ
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ
ታድማ በመዘንበልዋ
ዐፅምሽ በትንሣኤ ነፋስ
ደምሽ በነፃነት ሕዋስ
ሲቀሰቀስ ትንሳኤዋ
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ
ብር ትር ሲል ጥሪዋ
ድው-እልም ሲል ጋሻዋ
ሲያስተጋባ ከበሮዋ
ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ
ያባ መቻል ያባ ዳኘው
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው
ያባ በለው በለው ሲለው
በለው-በለው-በለው-በለው!
ዋ!... አድዋ…
ያንቺን ጽዋ ያንቺን አይጣል
ማስቻል ያለው አባ መቻል
በዳኘው ልብ በአባ መላው
በገበየሁ በአባ ጎራው
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው
በለው ብሎ በለው፣ በለው- በለው!
ዋ! … አድዋ …
አድዋ የትላንትናዋ
ይኸው ባንቺ ህልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመሥዋዕት ክንድሽ ዝና
በነፃነት ቅርስሽ ዜና
አበው ተነሡ እደገና፡፡
… ዋ! … ያቺ አድዋ
አድዋ ሩቅዋ
የዐለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
አድዋ…

© የአለም ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን
/ ዋ፦ ያቺ አድዋ!!