Monday, March 7, 2016

የጾም ዋጋ



ጾም ዋጋ የሚያሰጠው ከምግብ በመከልከል ብቻ ሳይሆን ከኃጢአት ሥራዎችም መራቅ ነው፡፡ ሥጋ በለመብላቱ ብቻ የጾመ የሚመስለው ቢኖር በዚህ አንዳች ነገር አያገኝም፤ ጾሙ ብላሽ ወይም ከንቱ ናት፡፡ ትጾማለህ? በሥራህ ግለጠህ አሳየኝ፡፡ በምን ዓይነት ሥራ ይገለጣል ትለኝ እንደሆነ ለደሃ ራራለት እዘንለት፡፡ የተጣለህን ታረቀው፣ በባልጄራህ ክብር አትቅና፡፡ መልከ መልካም ሴት ስታይ ውበቷ ሳይማርክህ እለፋት፡፡ ጾም አፍህ ብቻ ሳይሆን ዐይንህ፣ ጆሮህ፣ አፍንጫህ፣ እግርህ፣ እጅ፣ በአጠቃላይ መላ ሕዋሳትህ መጾም አለባቸው፡፡
እጆቻችን ከቅሚያና ከንፍገት በመንጻት ይጹሙ፡፡ እግሮቻችን ወደ ሕገ ወጥ ድርጊቶችና ተግባራት ከመሮጥ ታቅበው ይጹሙ፡፡ ዐይኖቻችን ቆነጃጅት ጋር መቦዝን ወይም ለሀይማኖት የማይመቹ እንግዳና ማራኪ ነገርችን ማየትን በመተው ይጹሙ፡፡ ዐይን የሚጠግበው በማየት ነው፡፡ ነገር ግን የምናያቸው ነገሮች ሕገ ወጥ፣ የተከለከሉና ለክርስትና የማይበጁ ከሆኑ ጾማችን ይበላሻል፡፡ በአጠቃላይ ነፍሳችን ምቾትን ታጣለች፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ጥሩና መልካም ነገሮችን የምናያቸው ከሆነ ጾማችንን እናስጌጣለን፡፡ በጾም ምክንያት ከተፈቀደልን ምግብ እንታቀባለን፡፡ በዐይናችን ግን የተከለከለውን ሁሉ እንደስሳለ፡፡
ሥጋ አልበላህም? በዐይንህ አትዳራ፤ አትሰስን፡፡ ጆሮም ይጹም፡፡ የጆሮ ጾም ክፉን አለመስማት ነው፡፡ ሐሰተኛ ወሬ አትቀበል፡፡ አፍ ከአሳፋሪ ንግግሮችና ስድብ ይጹም፡፡ ወንድሞቻችንን እያማን ከዶሮና ዐሣ ብንጾም ምን ይረባናል? ሃሜተኛ የወንድሙን ሥጋ ይበላል፤ ክፉ ተናጋሪም የባልንጄረውን አካል ይነድፋል፡፡ ስለዚህም ቅ/ጳውሎስ እንዲህ ያስጠነቅቃል፡-ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱና ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ ገለ. ፭፥ ፲፭፡፡
ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ

No comments:

Post a Comment