Monday, February 22, 2016

ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፡፡ ዮናስ ፩፥ ፪ ክፍል ፩


ይህ ከእግዚአብሔር ለሰው ልጅ የተሰጠ ትእዛዝ ነው፡፡ ለነቢዩ ዮናስ የተሰጠ የሕይወት አድን መመርያ፣ ሰውን የማዳን ተልእኮ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ዓላማ ሰውን ማዳን ነው፡፡ ዮናስ ማለት ርግብ፣ የዋህ ማለት ነው፡፡ ዮናስ የዋህ ነቢይ ነው፡፡
ነነዌ ከአንድ መቶ ሃያ ሺ በላይ ሕዝብ የሚኖርባት ታላቅ ከተማ ናት፡፡ ነነዌ በነቢያት ብዙ ሸክም (ኃጢአት) የተነገረባት፣ የእግዚአብሔር ቁጣ የተቃጣባት የኃጢአት አምባ ናት፡፡

Friday, February 19, 2016

ለክርስቲያን መከራ ጌጡ እሳት ሽልማቱ ነው፡፡


አባቶቻችን አብያተ ክርስቲያናትን አንጸው ታቦት አስቀርጸው ኢትዮጵያ ሀገራችን በረከተ እግዚአብሔር እንድታገኝ አድርገው ለዓለም ሰላም ሲጸልዩ ኖረዋል፡፡ አሁን አሁን ግን የእሳት ልጅ አመድ እንዲሉ ለሀገር ፍቅር ለወገን ክብር የሌላቸው፣ ሰላም የራቃቸው፣ ፍጹም ኢትዮጵያዊነት የማይሰማቸው፣ በሴይጣናዊ አስተሳሰብ የተቃኙ ታሪክ በራዥ ቅርስ አጥፊዎች አብያተ ክርስቲያናትን ማቃጠል ጀምረዋል፡፡ ድንቁርናቸው ነው እንጂ እነዚህ ወገኖች የሚጎዱት ክርስቲያኖችን ሳይሆን ራሳቸውን ነው፡፡ የሚያፈርሱት የእግዚአብሔርን ቤት ሳይሆን ሀገርን ነው፡፡ አይ አለማወቅ! ለክርስቲያን እኮ እሳት ብርቁ አይደለም፡፡ መከራ ጌጡ፣ እሳት ሽልማቱ፣ ስደት ሕይወቱ ነው፡፡

Friday, February 12, 2016

በማን ድግስ ማን ይጋብዛል?

የሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ጥር ፳፱ ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ከብሔራዊ ቤተ መዛግብት ወመዘክር ወደ ነባር ቦታው በክብር ሲመለስ ቅዱስ ፓትርያርኩ የክብር እንግዳ ሆነው በሥነ ሥርዓቱ ላይ መገኘታቸውን ከሪፖርተር ጋዜጣ ረቡዕ እትም የካቲት ፪ ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ገጽ ፴ ላይ ስመለከት አግራሞት ፈጠረብኝ፡፡ ግራም ተጋባሁ፡፡
ጋዜጣው ሀውልቱ ከብሔራዊ ቤተ መዛግብት ወመዘክር ተነስቶ ወደ አራዳ ቅ/ጊዮርጊስ ወይም ወደ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ አደባባይ ሲጓዝ የነበረውን ሥነ ሥርዓት እንደሚከተለው ይተርካል፡፡

Tuesday, February 9, 2016

የሰው ፡ ወርቅ ፡ አያደምቅ



             
ማነቃቂያ

ያገሩን ፡ ቋንቋ ፡ ተምሮ ፡ ንባብ ፡ ከጽፈት ፡ ሳያውቅ ፡ ያማርኛን ፡ ግስ ፡ በማቃለል ፡ ግእዝን ፡ ደግሞ በመናቅ ፡ የፈረንጅ ፡ ፊደል ፤ አትንቶ ፡ ምንም ፡ ቢያስተውል ፡ ቢራቀቅ ፡ የሰው ፡ ወርቅ ፡ አያደምቅ ፤ አያደምቅም ፡ የሰው ፡ ውርቅ ፡፡

 ደስታ ተክለ ወልድ ( ያማርኛ መዝገበ ቃላት)