Monday, May 25, 2015

የመሥዋዕቱ በግ የት አለ ? ዘፍ. ፳፪፥፯

                                                                                                     በዲ/ን ዓለማየሁ ሀብቴ
              ክፍል ፩  
መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የኃጢአት ማስተሥርያ ነው፡፡ በዘመነ ብሉይ ሰው በአምላኩ ፊት ስለበደሉ መጸጸቱን (ንስሓ መግባቱን) ለማሳየት፣ ሞገስ ለማግኘት፣ እምነቱን ለመግለጽ፣ ምስጋና ለማቅረብ፣ ፍቅሩን ለማሳየት መሥዋዕት ያቀርብ (ይሰዋ) ነበር፡፡ በወቅቱም ለመሥዋዕት ከሚቀርቡት እንስሳት መካከል በግ ዋነኛው ነበር፡፡
አቤል በሕገ ልቡና ተመርቶ፤ በፍፁም እምነት፣ በንፁህ ሕሊና፣ በበጎ አእምሮ ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ያቀረበው፤ አምላኩም ያሸተተለት ተወዳጅ መሥዋዕት ቀንዱ ያልከረከረ፣ ፀጉሩ ያላረረ፣ ጥፍሩ ያልዘረዘረ ፀዓዳ በግ ነው፡፡ ዘፍ. ፬-፭ አቤልም በግ ጠባቂ ነበረ (አርቢ)፤ ቃየንም ምድርን የሚያርስ (ገበሬ) ነበረ፡፡ ከብዙ ቀን በኋላም ቃየን ከምድር ፍሬ ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን አቀረበ፤ አቤልም ደግሞ ከበጎቹ በኩራትና ከስቡ አቀረበ፡፡ እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ፤ ወደ ቃየንና ወደ መሥዋዕቱ ግን አልተመለከተም፡፡

Thursday, May 21, 2015

ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈፅሞ ስለ ተገለጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ ... ይሁ. 1፥ 3::

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
 አስተበቊዓክሙ ከመ ትትወከፍዋ ለሃይማኖት እንተ ተውህበት ሎሙ ለቅዱሳን፡፡ ይሁ. 1 3
በመምህር ጽጌ
ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈፅሞ ስለ ተገለጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ:: የሃይማኖት ስር መሠረቱ በሰብአዊ ፍጡር ምርመር የተገኘ፣ በስነ መለኮት ምሁራን አስተያየት ተሰጥቶበት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ፣ እየተመረመረ ሲወርዱ ሲዋረደ እኛ ዘንድ የደረሰ የእምነት ዕቃ አይደለም፡፡ ወይም ጥላ እሸት ቀቢዎች እንደሚያሰራጩት ውስጡን ሳናውቀው ከውጪ አገር በአደራ የመጣልን የታሸገ ፓስታ አይደለም፡፡ሃይማኖትሰ፣ ጥይቅት፣ ይእቲ፣ ለዘይሴፈዋይላታልና ዕብ. 111፡፡ ይህን ለመረዳት እግዚአብሔር ዓይነ ልቡናችንን ያብራልን፡፡ በማስተዋል እየፃፍኩ ነው እናንተም አስተውላችሁ አሜን! በሉ፡፡ ይህ ማለት ሳይገባችሁ እንደ መፈክር በሚያስተጋባ ድምፅ በአሜንታ አጅቡኝ ማለቴ አይደለም፡፡ በማስተዋል አሜን! አላችሁ? እሺ ስለ ሃይማኖት እያወራን ነው፡፡

ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም ዮሐ.3፥13፡፡



አልቦ ዘዓርገ ውስተ ሰማይ ዘእንበለ ዘወረደ እምሰማይ ወልደ ዕጓለመሕያው ዮሐ.313


የተወደዳችሁ የማኅቶት አንባብያን እንኳን ለብርሃነ ለዕርገቱ በሰላም አደረሰችሁ አሜን! እናሆ ስለጌታችን ዕርገት ቤተ ማርያም የተባሉ ሰው ከማኅበረ ቅዱሳን ወስደው ፌስ ቡክ ላይ የለጠፉት ቆንጆ ትምህርት ይዤላችሁ ቀርቤአልሁ፡፡ አምላክ ዓይነ ልቡናችሁን ያብራላችሁ፡፡
ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፡፡ እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው፡፡ ይህ ኃይለ ቃል ክብር ምስጋና ይግባውና ስለጌታችን፣ አምላካችን፣ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት መውረድ ከድንግል ማርያም መወለድ እና የሰውነቱን ሥራ ጨርሶ በክብር ወደ ሰማይ ማረጉን የሚገልጽ ነው፡፡ እንደሚታወቀው አምላካችን ስለሁለት ዐቢይ ጉዳዮች ሰው ሆኗል፡፡

Tuesday, May 19, 2015

ሰው ብቻ አትሁኑ፡፡

በመጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ

ሰው ብቻ ማለት ምንድን ማለት ነው? ብዬ ሳስብ፤ የሚበላ፣ የሚጠጣ፣ በሚለብሰው ልብስ፣ በሚነዳው መኪና የኑሮን ስኬት የሚለካ ማለት ነው። እስከ ሞት የሚኖር ማለት ነው እንደ እንስሳ። ታላቁ ሊቅ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይላል፡፡ ሰው እግዚአብሔር ሲለየው ጠባዩ እንደ አራዊት፤ አመጋገቡ እንደ እንስሳ፣ ሆኖ መልኩ ብቻ የእግዚአብሔር ሆኖ ይቀራል። በጣም ቀለል ባለ አገላለጽ ሲም ካርዱ የወጣ ጥሪ የማይቀበል ሞባይል ማለት ነው። ለጉትቻ ማንጠልጠያ ብቻ የተሠራም ጆሮ አለ።