Thursday, May 21, 2015

ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈፅሞ ስለ ተገለጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ ... ይሁ. 1፥ 3::

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
 አስተበቊዓክሙ ከመ ትትወከፍዋ ለሃይማኖት እንተ ተውህበት ሎሙ ለቅዱሳን፡፡ ይሁ. 1 3
በመምህር ጽጌ
ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈፅሞ ስለ ተገለጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ:: የሃይማኖት ስር መሠረቱ በሰብአዊ ፍጡር ምርመር የተገኘ፣ በስነ መለኮት ምሁራን አስተያየት ተሰጥቶበት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ፣ እየተመረመረ ሲወርዱ ሲዋረደ እኛ ዘንድ የደረሰ የእምነት ዕቃ አይደለም፡፡ ወይም ጥላ እሸት ቀቢዎች እንደሚያሰራጩት ውስጡን ሳናውቀው ከውጪ አገር በአደራ የመጣልን የታሸገ ፓስታ አይደለም፡፡ሃይማኖትሰ፣ ጥይቅት፣ ይእቲ፣ ለዘይሴፈዋይላታልና ዕብ. 111፡፡ ይህን ለመረዳት እግዚአብሔር ዓይነ ልቡናችንን ያብራልን፡፡ በማስተዋል እየፃፍኩ ነው እናንተም አስተውላችሁ አሜን! በሉ፡፡ ይህ ማለት ሳይገባችሁ እንደ መፈክር በሚያስተጋባ ድምፅ በአሜንታ አጅቡኝ ማለቴ አይደለም፡፡ በማስተዋል አሜን! አላችሁ? እሺ ስለ ሃይማኖት እያወራን ነው፡፡

 ጠቢቡ ሰሎሞን በመጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ 8 9 ከሊቃውንትም ኤጲፋንዮስና ዲዮስቆሮስ በቅዳሴአቸው ስለ ጥበብ ርቀትና ምጥቀት ሲፅፉ አይቴ ብሔራ ለጥበብአይቴ ማህደራ ለጥበብ፣ አይቴ ደወላ ለጥበብ፣ ወአይቴ ተረክበ አሰረ ፍኖታ፣  ወመኑ አደወ ባሕረ ወተሳየጣ በወርቅ ቀይሕየጥበብ አገሯ ወዴት ነውማደርያዋ የት ነውአድራሻዋስ ወዴት ነውኮቴዋስ የት ተገኘባሕርን ተሻግሮ በቀይ ዕንቊ የገዛትስ ማንነው? ብለው ፅፈዋል፡፡ በጥያቄ እንጀምርና ሐዋርያው በገለጠው መሠረት ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ብቻ የተገለጠች ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ፃድቃን፣ ሰማዕታት የሞቱላት፣ የተሰውላት፣ የተጋደሉላት ሃይማኖት መገኛዋ የት ነው? መቼ ተፈጠረች? ከየትስ መጣች? መልካም ይህን ጥያቄ ለመመለስ የዓለም ሊቃውንት የተለያየ መላምልት ሰንዝረው አልፈዋል፡፡ መላእክት ሲፈጠሩ፣ አልያም አዳም ሲፈጠር ተፈጥራ በፍልስጥኤም ምድር  ወይም ከመካከለኛ ምስራቅ  እንደተገኘችና ከዚያም በንግድ ልውውጥ እንደ መጣች፤ እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐሳቦች እንደምታውጠነጥኑ ይታወቃል፡፡ ግምታችሁ መፅሐፍ ቅዱሳዊ ድጋፍ ባይኖረውም የብዙ ሰዎች ሐሳብ ስለ ሆነ በኢምሁራን ሳምባ መተንፈሳችሁን ታስታውቃላችሁ፡፡ ሃይማኖት በእጅ ብልጫ ሳይሆን ጥቂት ሰዎች ብቻ በሚገቡባት በጣም በጠበበች በር ነው የምትገኘው ማቴ.714፡፡
አንድ ነገር ላስታውሳችሁ፡፡ ተዘከሩ ቃለ ዘነገሩክሙ ቀዲሙ ሐዋርያቲሁ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት የተነገረውን ቃል አስቡ ይሁ.117፡፡ ይህ የምጽፍላችሁ ጽሑፍ የሐዋርያት ወይም የኋላ ሊቃውንት አስተምህሮ ነው? ወይስ ልብ ወለድ? ወይስ ዘመን ያመጣው? ብላችሁ መጠርጠረና መመርመር አለባችሁ፡፡ ሃይማኖት በየቀኑ፣ በየዘመኑ መልክዋን፣ ባህልዋን እየለወጠች፣ አስተምህሮዋን እየቀያየጠች፣ የምትገለጥ የሆነች ግራ የምታጋባ ነገር አይደለችም፡፡ ወደ ጥያቄው ልመልሳችሁ፡፡ ሃይማኖት እንተ እምኀበ አብ ተፈጥረት፣ ኀበ ወልድ ታበፅሕ፣ ወኀበ መንፈስ ቅዱስ ትትፌፀም ሃይማኖትስ በአብ ዘንድ የነበረች፣ ወደ ወልድ የምታደርስ፣ በመንፈስ ቅዱስ የተፈፀመች ወይም የመገለጥዋን ፍፃሜ በመንፈስ ቅዱስ ያገኘች ናት”፡፡ አዎን ሃይማኖት በእግዚአብሔር አብ ህሊና የነበረች፣ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ (ምስጢረ ሥጋዌ) ጠርታ ጎልታ የታወቀች፣ በበዓለ በርደተ መንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በፅርሐ ጽዮን በሐዋርያት ጉባኤ የፀደቀች፣ ሙሉ በሙሉ የተደመደመች ናት እንጂ በበራልኝ፣ ተገልጠልኝ፣ ነገረኝ፣ ተነገረኝ የተገኘች፣ በሥጋዊ ደማዊ ፍልስፍና የተዋቀረች፣ የሰብአዊ ሐሳብ ጥርቅም አይደለችም፡፡ ጥንት በአምላክ ህሊና የነበረች፣ አሁን ያለች፣ ደግሞ ያለ መበረዝ ያለ መከለስ በፍፅምና ለዘለዓለም የምትኖር ናት፡፡ አሜን! የሃይማኖት መገኛ ማንም ማን ሊያየውና ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ውስጥ ያለ እግዚአብሐር እንጂ(1ጢሞ. 616) በየስኪሪኑ(ሰሌዳ) የሚታየው ነጪ አውሮፓዊ ወይም ጥቁር አፍርካዊ ፈዋሽና ሰባኪ ነኝ ባዩ አይደለም፡፡ ሃይማኖት የተሰበከችው የተሐድሶ አራማጆች ከተነሱበት 16-20 / ጀምሮም አይደለም፡፡ ሃይማኖት የተሰበከችልን በለቤቱ ራሱ ጌታችን ባስተማራቸውና በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቀው ከብልየት በታደሱ መከራን እየተቀበሉ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው በሰይፍና በስለት ያለፉ ዓለም ያልተገባቻቸው ሐዋርያት ነው ዕብ .1137፡፡ የሃይማኖት መሠረት ክርስቶስ ነው 1ቆሮ. 311፡፡ ዛሬ በዚህ ርዕስ ለመጻፍ የተነሳሁበት የሃይማኖት ጉዳይ ነው፡፡ ምናልባት ስታነቡእምንት እንጂ ሃይማኖት የለንም እምንት እንጂ ሃይማኖት አያፀድቅምየሚትል አረማዊት አስተሳሰብ ከጎረቤት የቀላወጣችሁት ወሬ ካለች ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈፅሞ የተገለጠ ሃይማኖት የሚለውን ይሁ.13 በማስዋል አንብቡና የሃይማኖት ምንነት ተረዱ፡፡ አዎን መጽሐፍ ቅዱስ  ልዩ ልዩ በሆነ እንግዳ ትምህርት አትወስዱ ይለናል ዕብ. 139፡፡ ልብ በሉ የሃይማኖት መሠረት ከሌለንእንግዳ በሆነ ትምህርት ልንወስድ እንችላለንእንግዳ ሃይማኖት ነባር አይደለም፣ ከእግዚአብሔር ጋር አልነበረም፣ አይታወቅም፣ ለሰውም ለአገሩም በዳ ነው፣ አዲስ ነው፣ የሰው ሥርዓት የሰው ንድፈ ሐሳብ ነው፡፡ ለዚህ ነው ‹‹በሐዋርያት ቃል ቀድሞ የተነገረውን አሳቡ ያልኩት›› በእርግጥ በሐዋርያት ዘመን እንዲሁም በዘመነ ሊቃውንትም በዓይነቱ ልዩ የሆነ እንግዳ ትምህርት ተከስቶ ነበር፡፡ እንደ አሁኑ በየጓደው ባይሆንም፡፡ በዚህም ሐዋሪያትም ሆኑ ሊቃውንት በየጊዜው ለተነሱ የሐሰት አስተማሪዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ውሳኔና ቀኖና ይሰጡ ነበር፡፡ወሰኑ ወሠርዑ ሃይማኖተእንዲል፡፡ ሃይማኖታዊ ድንበር እንዳይጣስ በተለይ ስህተትን ለመቃወም ከታወቁ የጥንት ሲኖዶሶች (ጉባኤዎች) ሶስቱ የሚከተሉት ናቸው፡፡
 1. የሐዋርያት የእምነት አቋም (ፀሎት ሃይማኖት ዘሐዋርያት)
2. የሶስት መቶ ሊቃውንት (ፀሎት ሃይማኖት ዘኒቅያ)
3. የአትናቴዎስ የእምነት መግለጫ (ፀሎት ሃይማኖት ዘአፍራቂያ/ዘአፍሪካ/)
 እነዚህ ሁሉ በሊቃውን ታይተው ውሳኔ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያላቸው መሆኑን በተባረኩ አባቶቻችን ተረጋግጠዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሔዋን አዳምን ሳታማክር ዕፀ በለስ በልታ አብልታ እንደበላችው፣ ስታ እንዳስተችው፣ ሰዎች ከሃይማኖት አስተማሪዎቻችን ሳይማከሩ፣ ሳይማሩ፣ በሐሰተኞች አስተማሪዎች ከየመንገዱ እየተጠለፉ ነው፡፡ ሐዋርያውክፉዎች ሰዎትና አታላዮች ኢያሳቱና እየሳቱ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ አንተ ግን በተማርህበትና በተረደህበት ፀንተህ ኑር” 2ጢሞ. 313-16 እንዳለው ባለንበት ሃይማኖት ፀንቶ መኖሩና መማሩ መወያየቱ ጠቃሚ ነው፡፡ ይህ የሃይማኖት መበጧጠስ ያፈራው ለመፅሐፍ ቅዱስ ካለ መታዘዝ የተነሳ ነው፡፡ ሐዋሪያው ያዕቆብ 31 ላይ እንዲህ ፅፏል ’’ወንድሞች ሆይ ከእናንተ ብዙዎች አስተማሪዎች አይሁኑ የባሰውን ፍርድ እንድንቀበል ታውቃለችሁናአስተማሪዎች ሲበዙ ሐዋርያው እንዳለው በዓይነቱ ልዩ የሆነ ትምህርት መቀረፅ አይቀሬ ነው፡፡ ሰውን ቀልብ ሊሰብ የምችል ቀለል ያለፓልሲእንበለው? ለምሳሌ  ማሕተብ እንደ ኮተትፆምን መፆም እንደ ኩነኔ መቁጠር፣ ፀሎት መፀለይ ፕሮክራሲ እንደማብዛት፣ የመለእክተን ስም መጥራት ሰይጣን እንደ መጥራት ወዘተ የመሳሰሉትን ያስተምራሉ፡፡
በመሠረቱ የቤተ ክርስቲያናችን ቀኖናዎች በሙሉ መጽሓፍ ቅዱሳዊ ናቸው፡፡ ለእያንዳንዱ መጽሓፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ አለን፡፡ በእውነቱ ይህ ዓይነቱ ውንብድና በምዕመናን ላይ ገሃነማዊ ፍርድ ማስከተል ነው፡፡ህየንተ ቡራኬ መርገመ ወህየንተ ስርየት ኃጢአት እሳተ ገሃነምበቡራኬ ፈንታ መርገምን በኃጢአት ስርየትም ፈንታ ገሃነም እሳትንማለት እንጂ ይለናል፡፡ አንድ አንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በስመ ክርስትና የሚጠሩ በመሠረታዊ የክርስትና እምነት ማለትም በሐምስቱ አእማደ ምሥጢርና በሰብአቱ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን ካለመግባባት የተነሳ የተለያዩ በቁጥር አየናሩ እየጨመሩ 33,000 በላይ እንዳሉ ይጠቁማሉ:: 33,000 በላይ ይቅርና በዓለም ሁለት ሃይማኖቶች ቢኖሩ እንኳ አንዱ ሐሰት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስአሃቲ ሃይማኖትሃይማኖት አንዲት ናት ይላት የለም አፌ. 46፡፡ ይህ የሆበት ምክንያት 16-20 .. በተነሱ የተሃድሶ አራማጆች መጽሐፍ ቅዱስን ከተጻፈበት ዓለማና መንፈስ ውጪ በማውጣት እንደበራላቸው፣ እንደሻቸው፣ ከተሰመረለት መለኮታዊ መስመር ውጪ በተመርጐም ልጓም እንደ ሌለው እንዳልተገራ ፈረስ በአስተምህሮ ሲደናበሩ ለዚህ ክፍፍል ደርሰዋል፡፡ አዲሱ የእምነት እንቅስቃሴ እውነት ከሆነ ለምን 33 ተከፈፈል? ለምን በአንድ አስተምህሮ አይስማውም? ይህየቤት ሰጥቻችአለሁ፡፡ ክርስቶስ የመጣው እኮ በሃይማኖት አንድ ያደርገን ዘንድ ነው፡፡ ሊለየን፣ ሊለያየን፤ ሊበትነን፣ ሊበታትነን አይደለም፡፡ አንድ ባለ ቅኔመምህረ ኮነ በበደወሉ፣ ፊደላተ ዘኈለቈ ኩሉትርጉሙፊደላትን የቈ ጠረ ሁሉ በየአጥቢያው አስተማሪ ሆነብለው ሐዜኔታቸውን በቅኔ ገለፁ፡፡ እውነት ነው፡፡ ሳይማሩ ማስተማር፣ ሳይሰበኩ መስበክ፣ ሳይጠመቁ ማጥመቅ ከሁሉ የሚገርመው የዘፈን ከሴቶቻቸው እንኳ ተሸጦ ሳያልቁ፣ ለስድስት ወር እንኳ በወጉ ሰይማሩ ፓስተር፣ ሳይመገቡ መጋቢ ተብለው መጠራቱ ነው፡፡ ለነገሩማ እነሱ ምን ወግ አላቸው? ይህ በእግዚአብሔ ላይ ድፍረት ነው፡፡ አስተውሉይሴርዎን እግዚአብሔር ለከናፍሩ ጒሕሉት፣ ወለልሳን እንተ ተዓቢ ነቢበ፣ እለ ይብሉ ናዓቢ ልሳናቲነ ወከናፍሪነኒ ኃቤነ እሙንቱ፣ መኑ ውእቱ እግዚእነየሽንገላ ከንፈሮች ሁሉ እግዚአብሔር ያጠፋቸዋል፣ ታላቅ ነገርንም የምትናገረው ምላስ፣ ምላሳቸን እናበረታለን ከንፈራችን የእኛ ነው፣ ጌታችን ማነው የሚሉትን?” መዝ. 123-4፡፡ ሁሉም በአንድ የመጽሐፍ ቅዱስ መለከታዊ መመሪያ የሚመሩ ቢሆኑ ኑሮ ወደ እንዲህ ዓይነቱ አሳፋሪ መበታተን አይገቡም ነበር፡፡ በተለይ በአሁን ባልንበት በመጨረሻ ዘመን ሐሰተኞች አስተማሪዎች ሐሰተኞች ነቢያት 2ጴጥ.21 ማቴ. 2411 ሐሰተኞች ክርስትያኖች እንደ ሚነሱ መንፈስ ቅዱስ በግልጥ ነገሮናል 2ጢሞ. 31-3፡፡ እግዚአብሐር ምሥጢሩን አስቀድሞ ለባርያዎቹ ሳይነግር አንዳች አያደርሳምአሞ. 37፡፡ እስከ መጨረሻ በእምነቱ የሚፀና ግን እርሱ ይድናል ማቴ. 2412፡፡
 በመጀመሪያ በእግዚአበሔ በነበረች፣  ወደ ወልድ ወደ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምታደርሰው፣ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ በተገለጠች ሃይማኖት ፀንታችሁ ትጋዳሉ ዘንድ እግዚአብሔር ፅናቱን፣ አእምሮውን፣ ለብዎውን ይሰጣችሁ፡፡ ነፋስ በነፈሰ፣ ማዕበል በተነሳ፣ ጎርፍ በጎረፈ፣ ጊዜ መልህቅ እንደሌላት መርከብ ወደያና ወዲህ እንዳንገለባበጠን እምነታችን በዓለቱ በክርስቶስ ላይ መመስረት አለበት፡፡ በእውነተኛ ቃሉ ላይ መተከል አለብን ማቴ.724-27፡፡
 ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ

No comments:

Post a Comment