Friday, December 25, 2015

በእስራኤላውያን የነፃነት ትግል የመቃቢያን ሚና

ጤና ይስጥልኝ የማኅቶት ታዳሚያን እንደምን ዋላችሁ!
ዛሬ እንድ ወዳጄ መቃቢስ ማነው ልጆችስ አሉት ወይ ከሉትስ እነማን ይባላሉ መቃቢያን በእስራኤል የነፃነት ትግል ታሪክ ውስጥ ያለቸውስ ቦታ ምንድን ነው ብለው ለጠየቁኝ ጥያቄ አጭር ማብራርያ እነሆ ብያለሁ፡፡ መልካም ንባብ፡፡
በእስራኤላውያን የነፃነት ትግል የመቃቢያን ሚና
እስራኤል በውጭ ገዢዎች ስልጣን ስር በመውደቅ ረጅም ታሪክ አለት፡፡ መቃቢያንም በዚህ የታሪክ ጉዞ ውስጥ ጉልህ ሚና ነበራቸው፡፡

Friday, December 18, 2015

ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሳልሳዊ የኢትዮጵያ ጳትርያርክ

አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከጵጵስናቸው በፊት መጠሪያ ስማቸው አባ መልአኩ ሲሆን የተወለዱት  የንጉስ  ወልደ  ጊዮርጊስ ታማኝ  ወታደር ከነሩት አባታቸው ከወታደር ወልደ ሚካኤል አዳሙ እና አባታቸው ለውትድርና ጎጃም ሄደውካገቧቸው ባለቤታቸው ከወይዘሮ ዘውዲቱ ካሳ  በጎንደር    ላይ  ግዛት  ማኅ ደረ  ማርያም  ተብላ  በምትታወቀው  ገዳም  አካባቢ  ጋዥን  በምትባል ቦታ  ነው   
            ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሳልሳዊ የኢትዮጵያ ጳትርያርክ 


THE FAITH OF THE CHURCH

PART-I
Introduction
A member of the Oriental Orthodox family of Churches, the Church of Ethiopia shares with them in essence a common faith. This faith, the churches believes is derived from the apostolic heritage and borne witness to in the New Testament against the background of the Old Testament. It has been expounded by the fathers of the Church both in the ancient councils and in their teaching. It continues as a living reality in the church in its life of worship, preaching and discipline. In a word, then in the church of Ethiopia is a community which has inherited and which holds to the historic Christian faith as it has been handed down through the centuries. What is attempted here is, only to give a brief introduction to the faith of the Church of Ethiopia.

Friday, December 11, 2015

፲ቱ ማዕረጋት

ታሕሳስ 1 ቀን 2008 ..
መምህር ደጉ ዓለም
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ
የሐዲስ ኪዳን መምህር
ኩኑ ቅዱሳን እስመ ቅዱስ አነዘሌ.192
ቅዱሳን ማለት የተቀደሱ፣ የከበሩ፣ የተመሰገኑ፣ የተለዩ፣ የተመረጡ፣ ንጹሐንየሆኑ፣ የጠሩ….. ወዘተ ማለት ነው፡፡ ቅዱሳን በዚህ ስም የሚጠሩበት ከሰው ወይም ከምድራዊ ባለሥልጣን የተቸሩት አይደለም፡፡

Thursday, December 10, 2015

አማን መነኑ ሰማዕት ጠዕማ ለዛ ዓለም



በፋሽቶች ይሙት በቃ የተፈረደባቸው ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በችሎት ፊት ለብዙ ሰዓታት ቆመው ስለዋሉኖ ደከሞአቸው ስለ ነበር ለመቀመጥ ፈልገው ዳኛውን በትሕትናና በፈገግታ ጠየቁት። እንዲ ቀመጡም ፈቀደላቸው፡፡ በመጨረሻም የሞታቸው ፍርድ ከተነበበ በኋላ የፈረዱባቸውን ዳኞች ጸልየው በመስቀላቸው ባረኩዋቸው። ብፁዕነታቸው እስከ መቃብር አፋፍ ድረስ የፍርሃትና የድንጋጤ ምልክት ያይደለ ከልብ የሆነ ፍጹም ቆራጥነት ይታይባቸው ነበር፡፡
የሀገራቸው በጠላት መወረር የሕዝበቸው መገደልና መታስር የቤተ ከርስቲያናቸው መደፈር እስከ ሞት ያደረሳቸው እኒህ እውነተኛ ጳጳስ ለመገደል ሊወስዱ ጥይት አልፎ ሌላ ስው እንዳይጎዳ ግንብ ይፈለግ ጀመር፡፡ ሩቅ ባለመሔድ ከመካነ ፍትሑ 10 ሜትር ርቆ ግንብ ያለው መግደያ ቦታ ተገኘና ወደዚያ ተወስዱ። ከገዳዮቹም አንዱ ' ፊትዎን ለመሸፈን ይፈልጋሉገ ?' ሲል ጠየቃቸው፡፡ ' ይህ የአንተ ሥራ ነው ' ሲሉ ብፁዕነታቸው መለሱ ' ፡፡ ከመግደያውም ቦታ እንደ ደረሱ ወንበር ቀረበላቸውና ፊታቸውን ወደ ግንቡ ጀርባቸውን ወደ ሕዝቡ እድርገው እንዲቀመጡ ሆኑ።