አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከጵጵስናቸው በፊት መጠሪያ ስማቸው አባ መልአኩ ሲሆን የተወለዱት የንጉስ ወልደ ጊዮርጊስ ታማኝ ወታደር ከነሩት አባታቸው ከወታደር ወልደ ሚካኤል አዳሙ እና አባታቸው ለውትድርና ጎጃም ሄደውካገቧቸው ባለቤታቸው ከወይዘሮ ዘውዲቱ ካሳ በጎንደር ጠ ቅ ላይ ግዛት ማኅ ደረ ማርያም ተብላ በምትታወቀው ገዳም አካባቢ ጋዥን በምትባል ቦታ ነው ።
ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሳልሳዊ የኢትዮጵያ ጳትርያርክ
አባታቸው ወታደር ወልደ ሚካኤል ባደረባቸው ህመም ልጃቸው አባ መልአኩ ገና እርጥብ አራስ እያሉ በሞት ከዚህ አለም ተለዩ። በዚህም የተነሳ እናታቸው ወይዘሮ ዘውዲቱ ልጃቸው አባ መላኩ ትንሽ ጠንከር ሲሉ ይዘዋቸው ተመልሰው ወደ ጎጃም ተመለሱ እና አባ መልአኩ እዚያው ጎጃም ውስጥ ዘርዘር ሚካኤል በሚባል አካባቢ ማደግ ጀመሩ። ነገር ግን ብዙም የመጀመሪያ ትምህርታቸውን እንደጀመሩ እናታቸውም በሞት ከዚህ አለም ይለዩና ተመልሰው የአባታቸው ዘመዶች ወደሚገኙበት ቦታ ወደ ጎንደር ተመለሱ። ዘመዶቻቸውም እዚያው አካባቢ ተዋቂ መምህር ለነበሩት መሪ ጌታ ወርቅነህ ሠጧቸው። በዚያም ፊደል ከቆጠሩ በሇላ ወደ ደብረ ታቦር ተሻግረው እናቲቱ ማርያም በተባለችው ደብር ያስተምሩ ከነበሩት አለቃ ቀለመወርቅ ዘንድ ሔደው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀቁ። ከዚህም በሇላ ወደ አዲስ አበባ መጥተው በወቅቱ የኢትዮጵያ ጳጳስ ከነበሩት ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ መዓረገ ዲቁናን ተቀበሉ። ከዚያም ወደ ማኅደረ ማርያም ተመልሰው በዲቁና ሲያገለግሉ ቆዩ።
አባ መልአኩ ህይወታቸው በቤተ ክርስትያን ትምህርት አጎልምሰው በትኅርምትና እግዚአብሔርን በህይወታቸው ሙሉ በማገልገል ሊኖሮ በመወሰን ከጏደኞቻቸው ጋር ቅኔ ለመማር ወደ ጎጃም ይሄዳሉ። በዚያም በእናታቸው ሃገር አጠገብ ወደሚገኘውና የረዝ ሚካኤል ወደ ተባለው ቦታ መምህር ልሳነ ወርቅ ከተባሉ መምህር ዘንድ ቅኔንና ዜማን ለስምንት አመታት ያህል ተማሩ።
የዜማውንና የቅኔውን
ትምህርት በሚገባ ካጠናቀቁ በኋላ በተማርኩት ደግሞ ጥቂት ላገልግል በማለት ወደ ደብረ ታቦር ሔዱ። ይሁን እንጂ ወዲያውኑ የኢጣልያ ፋሺስት ጦር ኢትዮጵያን በግፍ በመውሪሩ እንዳሰቡት በሰላም ሊያገለግሉ አልቻሉም፡፡ በመሆ ኑም የአገልግሎት አሳባቸውን በመተው ራቅ ወዳለ ቦታ ሔደው በብሕትውና እየኖሩ ለመማር ወሰኑ፡፡ ይህንን ውላኔያቸውን ተግባ ራዊ ለማድረግ የሚሔዱበትን ሀገር ለመወሰን ሲያወጡ ሊያወርዱ እና የጓደኛቻቸውን ምከር ሲጠይቁ አንድ ጓደኛቸው በደቡብ ኢትዮጵያ ወላይታ አካባቢ አጎቱ በመንግሥት ሥራ ተሠማርቶ እንደ ሚኖርና አካባቢው በ13ኛው ክፍለ ዘመን ጻድቁ አቡነ ተከለ ሃይማኖት የተጋደሉበት፣ እንደ ደብረ መንክራት አቡነ ተከለ ሃይማኖት ዓይነት ታላላቅ ገዳማት እንዳሉበት፣ ቦታው በጥምቀት የቅድስት ሥላሴን ልጅነት ያላገኙ ሰዎች የሚበዙበት በመሆኑ ለብሐትውናና ለአገልግሎት የሚመች መሆኑን መክሮ አብረው ቢሔዱ ለጊዜው አጎቱ ቢት አንደሚያርፉ ይነግራቸዋል፡፡ ቅዱስነ ታቸውም የጓደኛቸውን አሳብ ተቀብለው በ1926 ዓ፡ም ሁለቱም ወደ ወላይታ ጉዞአቸውን ጀመሩ፡፡
አድካሚ ከሆነው ከብዙ ቀናት የእግር ጉዞ በኋላ ወላይታ ደርሰው ከጓደኛቸው አጎት ቤት ዐረፉ፡፡ አካባቢውን እስከሚላመዱ በእንግድነት ከቆዩ በኋላም ዝናው ከጎንደር ስቦ ወዳስመጣቸው ደብረ መንከራት አቡነ ተከለ ሃይማኖት ገዳም ገቡ፡፡ እግዚአብሔር እንደነ ጻድቁ አቡነ ዜና ማርቆስና ጻድቁ አቡነ ተከለ ሃይማኖት በአካባቢው ሥራ እንዲሠሩ መርጧቸዋለና ወደ ገዳሙ ሲገቡ በቦታው ረዘም ላለ ጊዜ የቆዩትን አለቃ ደስታ የተባሉትን ባሕታዊ አገኙ፡፡ ከእሳቸ ውም ጋር በአንድ በአት ተወሰነው መኖር ጀመሩ፡፡

ባሕታዊ አባ መላኩ በወላይታ እየተዘዋወሩ በሚያስተምሩመት ወቅት
ቅዱስነታቸው በደብረ መንከራት ገብተው ጥቂት ከቆዩ በኋላ የገዳሙ አበ ምኔት ከነበሩት መምህር ወልደ ኢየሱስ የቅዱሳት መጻሕፍትን ትርጓሜ በተለይም የማር ይስሐቅንና የመጻሕፍተ ሊቃውንትን ትርጓሜ በጥልቀት ተማሩ፡፡ ቅዱስነታቸው ከመማር ጋር በነበራቸው የቁም ጽሕፈት ችሎታ በመምህራቸው ታዝዘው ቅዱሳት መጻሕፍትን አየጻፉ ለገዳሙ ማኅበር እንጺዳረስ አድርገ ዋል፡፡ በዚህ ዓይነት የትዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢር ሲመረምሩና ሥርዓተ ገዳምን ሲያጠኑ ከቆዩ በኋላ በዚያው መዓረገ ምንኩስናን ተቀበሉ፡፡ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ መጥተው ከግብፃዊው ብፁዕ አቡነ ቁርሎስ መዓረገ ቅስናን ተቀብለው ወደ በአታቸው ተመለሱ፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተከለ ሃይማኖት ወደ ገዳማቸው ከተመለሱ በኋላ በጾም በፀሎት፣ በስጊድና በትጎርምት በገድልና በልዩ ልዩ ትሩፋት ተወሰነው አስከ 1940 ዓም ድረስ በአታቸውን አጽንተው ቆዩ፡፡ ይህም የተባሕትዎ ጊዜ ከፈጣሪያቸው ከአግዚአ ብሔር ልዩ ጸጋና በረከት የተቀበሉበትና ለወደፊት ዓላማቸው ሁሉ መመሪያ ያገኙበት ወቅት ነበር፡፡
በዚህ ዓይነት ለዓመታት በፍጹም ትኅርምት አና ተጋድሎ አንደ አባቶቻቸው አግዚአብሔርን በጸሎት ከለመኑ በኋላ በ1940 ዓ ም በአታቸውን በዚያው ገዳም አድርገው በአውራጃው ልዩ ልዩ ቦታዎች በመዘዋወር ማስተማር ጀመሩ፡፡ ቅዱስነታቸው በሚያስ ደንቅ ሁኔታ በአውራጃው ውስጥ በሚገኙት ሰባት ወረዳዎች አየተዘዋወሩ ሲያስተምሩ ከህገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ዘንድ በአካባቢው እንዲንቀሳቀስ የፈቃድ ደብዳቤ ከማግኘታቸው በስተቀር የተቆረጠላቸው ደመወዝ የተሰፈረላቸው አህል አልነበረም፡፡ በቅዱስነታቸው ትምህርት ከሦስት መቶ ሺህ (300,000) በላይ የሆኑ አማንያን አምነው እንደ ተጠመቁና የክርስቶስ ተከታዮች አንደ ሆኑ ይነገራል፡፡ በጣዕመ ስብከታቸው ይህንን ያህል ምአመን ካፈሩም በኋላ በቤተ መንግሥቱ እ ውቅና የነበረውንና በአካባቢው የሚገኙ ሰባት አውራጃዎች ተወካዮችን በአባልነት የያዘ 'የመገበሪያ ቦርድ' የተሰኘ አካል በማቋቋም የአካባቢው ሕዝቦች ገንዘብ እንዲያዋጡ በማገድረግ፣ ከዚህም ጋር የአካባቢውን የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ማፋጠንን ቀዳሚ ዓላማው ያደረገውን 'ብርሃነ ሕይወት' የተሰኘ ግብረ ሠናይ ድርጅት አቇቁመው የሚከተሉትን መንፈሳዊና ማህበራዊ ተቇማት አሰርተዋል።

- ምአመናኑ
አየተሰበሰቡ የሚጸልዩባቸውና ምሥጢራተ ቤተ ከር ስቲያንን የሚቀበሉባቸው በሁሉም ወረዳዎች 65 አብያተ ከርስ ቲያናትን አሠርተዋል፡፡ እንዲሁም ልጆቻቸው መንፈsሳዊውንና ሥጋ ዊውን ትምህርት የሚማሩባቸውን 24 ትምህርት ቤቶችን አቋቁመ ዋል።
- በወላይታ
ሶዶ ከተማ በደብረ መንከራት
ፃድቁ አቡነ ተከለ ሃይማኖት ገዳም አካባቢ 11 ከፍል የድኩማን ቤት
በማሠራት ራሳቸውን ለመርዳት የማይችሉ ድኩማን ምግብ
፣ ልብስና መጠለያ እንዲያገኙ በማድረግ ሐዋርያዊ ግዳጃቸውን ተወጥተዋል፡፡
- በዚሁ
ከተማ ውስጥ ለ400 ያላነሰ ሕዝብ
በአንድ ጊዜ መያዝ የሚችል 'የወጣቶች የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር
አዳራሽ' የተሰኘ መሰብሰቢያ አዳራሽ አሠርተው በአገልግሎት ላይ
ይገኛል፡፡
- አንድ
ክሊኒክ በዚሁ ክተማ ውስጥ አቋቁመው
ሕዝቡ አንጺጠቀምበት አድርገዋል፡፡
- ከከ ተማው ወጣ ብሎ በሚገኘው ቆንቶ በተባለው ቀበሌ በ1954 ዓም ባሠሩት አዳራሽ የቃጫና የልዩ ልዩ ጥበበ እድ ሥራዎችን በማቋቋም የአካባቢው ችግረኞች አየሠሩ ራሳቸውን አንጺረዱ እድርገዋል፡፡
በዚህ ዓይነት ሰፊ አገልግሎት ላይ ተጠምደው ቤተከርስ ቲያን የስጠቻቸውን ሐላፈነት በመወጣት ላይ ሳሉ ንጉሣዊው መንግሥት በወታደራዊው የደርግ መንግሥት ተተካ፡፡ በመሆኑም አንደ ቀድሞው ሁሉ ከሕዝቡ ገንዘብ ማሰባስብ አልቻሉዎ፡፡ በዚህ የተነሣ የልማት አገልግሎታቸው አንዳይቋረጥ
ወደ አዲስ አበባ አየመጡ ክቤተ ክርስቲያኗ ክምአመናን መለመን ጀመሩ፡፡ በዚህ ዓይነት በተወሰነ ደረጃ አየተንቀሳቀሱ እያለ ደርግ ሁለተኛውን የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን አላግባብ አስረ፡፡ ከቤተክርስትያኗ ቀኖና ውጭም ሌላ ፓትርያርክ እንዲመረጥ አዘዘ። ራሱ ባቋቋመው አስመራጭ ኮሚቴ አማካይነት ከየክፍሉ ለፓትርያርክነት እንዲመረጡ እጩ የሚሆኑ አባቶች እንዲጠቆሙ አደረገ። በዚህም ጥቆማ አባ መላኩ ሳያስቡትና በእግዚብሄር ፈቃድ አንዱ እጩ ሆነው ተጠቆሙ። በመጨረሻም የማጣሪያ ምርጫ አድርጎ ከተጠቆሙት አባቶች ውስጥ አምስቱ ብቻ እንዲቀሩ ካደረገ በኋላ ከ565 ወራዳ ዎች ሁለት ሁለት ተወካዮች አንዲላኩና በአምስቱ አባቶች ላያ የፓትርያርክነት ምርጫ ድምፅ እንዲሠጡ ጥሪ አደረገ። እነኝህም አምስቱ እጩዎች የሚከተሉት ነበሩ።
- አቡነ እንድርያስ (በወቅቱ የቤጌምድርና ሰሜን ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
- አቡነ ሰላማ (በወቅቱ የጋሞ ጎፋ ሊቀ ጳጳስ)
- አባ ተወልደ ብርሃን ወልደ ስላሴ (በወቅቱ የደብረ ቢዘን ገዳም አበምኔት)
- አባ ዮሐንስ ከሐሊ (ከእየሩሳሌም)
- አባ መላኩ ወ/ሚካኤል (በደብረ መንክራት ተክለ ሃይማኖት ገዳም ባኅት)
ባላሰቡት ሁኔታ ለዚህ ሃላፊነት የታጩት አባ መላኩም መንበሩ ለኔ አይገባኝም ብለው ተቃውመው እንደነበር ይነገራል። በዚህም የተነሳ ቅዱስነታቸው ቤተ ክህነት ውስጥ ተቀምጠው በዘበኛ እንዲጠበቁ ተደርጎ እንደበነበር ይነገራል። በአምስቱ እጩዎች ላይ ድምፅ እንዲሠጡ ከየወረዳው በተገኙ 909 ወኪሎች በተሠጠ ድምፅ መሰረት አባ መላኩ 317 ድምፅ በማግኘት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ሦስተኛው ፓትርያርክ ሆነው ተመረጡ። ሹመታቸውም እውን ይሆን ዘንድ ሐምሌ 11 ቀን 1968 ዓም መዓረገ ጵጵስና ተቀበሉ። በሇላም ነሐሴ 23 ቀን 1968 ዓም በቅዱስ ሲኖዶስ 'አባ ተክለ ሃይማኖት ሣልሳዊ የኢትዮጵያ ጳትርያርክ' ተብለው ተሾሙ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በጳትርያርክነት ዘመናቸው ለቤተክርስትያኗ ብዙ ተቃሚ ለውጦችን አምጥተዋል። ከነዚህም ለውጦች ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው።
- ቀደም
ስል በአቡነ ቴዎፍሎስ መሰረቱ ተ ጥሎ የነበረው የቃለ አዋድ ደንብ ማሻሻልና አንዳንድ ሁኔታዎችን ከወቅቱ ጋር አንድሄዱ ማድረግ
- በእያንዳንዱ አጥቢያ ቤተ ክርስትያን የሰንበት ትምህርት ቤት እንዲቇቇም ማድረግ
- ለአብነት መምህራን የወር
ደመዎዝ እንዲመደብላቸው በሲኖዶሱ ማስወሰውን፣ ተማሪዎችም ተመሳሳይ ድጎማ እንዲደረግላቸው ማድረግ
- በቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ ስድስት የካህናት ማሰልጠኛዎች አንዲቇቇሙ ማድረግ
- በተለያዩ
ጊዜያት 28 አጵስ ቆጶሳት
መሾም
- የሕፃናት
አስተዳደግ ጉባኤ ማእከል በቇቇም በየቤተክርስትያኖች በጥቅሉ አስከ 36 አጏለ ማውታ ማሳደግያዎች እንዲቇቇሙ ማድረግ
- ለዘመናት የም እመናን ጥያቄዎች ሆነው ሲያነጋግሩ የነበሩ ጉዳዮችን በማድመጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አንድሰጥባቸው ማድረግ። ከነዚህም ውስጥ ከሰባቱ አፅዋማት አንዱ የሆነውን የልደትና የጥምቀት ፆመ ገሃድ፣ ፆመ ነብያት የሚገባው በየዓመቱ ሕዳር 15 እንደሆነና ዓሣ በፆም ወራት አንደማይበላ ማስወሰን
- ልማትን በሚመለከትም ቅዱስነታቸው በሚሰጡት መመሩያ ያለምንም የሀይማኖት ልዩነት ኢትዮጵያውያን የሚገለገሉባቸው የእህል ወፍጮ ቤቶች አና ዳቦ ቤቶች አንዲቇቇሙ ማድረግ
ቅዱስነታቸው በፆም፣ በፀሎት፣ በቀዊምና በስግደት ተወስነው ቤተ ክርስትያንን ሲያስተዳድሩ ከቆዩ በሇላ በመጨረሻ ሰፊ አገልግሎትና ተጋድሎ ሲፈፅሙበት የቆዩበትን የደብረ መንክራት አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ገዳም በመጎብኘት ላይ ሳሉ በድንገት ታመሙ። ወደ አዲስ አበባ ባስቸኯይ መጥተው በዳግማዊ ምኒልክና የጦር ሀይሎች ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቦቆዩም ሊድኑ አልቻሉም። በመሁኑም ከ 12 አመታትየፓትርያርክነት አገልግሎት በሇላ ግንቦት 28 1980 ዓም በተወለዱ በ70 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። ቅዱስነታቸው መላ ዘመናቸውን በፆም፣ በፀሎትና በሰጊድ ያሳለፉት ከመሆናቸው ጋር ባደረባቸው ህመም የተነሳ ነፍሳቸው ከስጋቸው ስትለይ የሰውነታቸው ክብደት 25 ኪሎ ደርሶ እንደነበር ይነገራል። ቀብራቸውም በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ግንቦት 30 1980 ዓም ተፈፅሟል። የቅዱስነታቸው አገልግሎት ሲዘከር ይኖር ዘንድ አስከሬናቸው በክብር ባረፈበት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የመታሰቢያ ሀውልት ቆሞላቸው ዛሬም ይገኛል።
ምንጭ:-
1) ዜና ጳጳሳት ኢትዮጵያውያን (ዲ/ን መርሻ አለሀኝ)
2) ታሪካዊ መዝገበ ሠብ (ፋንታሁን እንግዳ)
ከSawasew የተወሰደ
No comments:
Post a Comment