Saturday, October 21, 2017
Tuesday, October 17, 2017
እመሰ ረሳዕኩኪ ኢየሩሳሌም ለትርስዓኒ የማንየ መዝ. ፻፴፮ ፥ ፭
በስመ
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን
ኢየሩሳሌም ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ፡፡
በዲያቆን ዓለማየሁ ሀበቴ
(ክፍል ፩)
ኢየሩሳሌም ማለት ሀገረ ሰላም
ማለት ሲሆን ፤ በቅዱስ መጽሐፍ ከነዓን ፣ ምድረ ርስት ፣ የተስፋ ምድር ፣ ማርና ወተት የሚፈስባት ሀገር ፣ የዳዊት
ከተማ በመባል ትታወቃለች[1] ፡፡
ኢየሩሳሌም እግዚኣብሔር ለአብርሀምና ለዘሩ ርስት አድርጎ የሰጠው
የተስፋ ምድር ናት ፡፡ እግዚአብሔርም አብራምን አለው ፡- ከአገርህ ፣ ከዘመዶችህም ፣ ከአበትህም ቤት ፣ ተለይተህ
እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ ፡፡ ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ ፣ እባርክሃለሁ ፣ ስምህንም አከብረዋለሁ ፤ ለበረከትም ሁን ፤ የሚባርኩህንም
እባርካለሁ ፣ የሚረግሙህንም እረግማለሁ ፣ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ ፡፡ አብራምም እግዚአብሔር እንደ ነገረው ሄደ
፡፡ ከካራን ወጥቶም ወደ ከነዓን ምድር ገባ ፡፡ እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ አለው ፡፡
ዘፍ. ፲፪ ፥ ፩- ፯ ፡፡
Friday, October 13, 2017
ወርኃ ጽጌ
ጾመ ጽጌ ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ያለው አንድ ወር ከዐሥር ቀን ወይም 40 ቀን ወርኃ ጽጌ፣ ዘመነ ጸጌ፣ ተብሎ ይጠራል፡፡ በነዚህም ቀናት በየቤተክርስቲያኑ የሚነበቡ ምንባባት፣ የሚዘመሩት መዝሙራት፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚቆመው ማኅሌት በጠቅላላው የሚነገረው ስብሐት እግዚአብሔር ሁሉ
ሰማይ በከዋክብት ምድር በጽጌያት አሸብርቀው የሚታዩ መሆናቸውን የሚገልጽ ነው፡፡
Saturday, September 9, 2017
መልካም አዲስ ዓመት !
እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም አሸጋገረን!
አዲስ ዓመት ሲመጣ መልካም
ምኞትንና ብሩህ ተስፋን ሰንቆ ነው፡፡ በአዲስ ዓመት ዓመቱ የዕድገት፣ የብልፅግና፣ የሰላም ዘመን ይሁንልን የምንባባለው ከዚህ መልካም
ምኞትና ብሩህ ተስፋ የመነጨ ነው፡፡
አዲስ ዓመትን ቤት እንዳፈራ
ዶሮ፣ በግ፣ … አርዶ በዓሉን ማክበር ብቻ ሳይሆን ሰው ራሱ ከዘመኑ ጋር አብሮ በአስተሳሰብ መታደስ በሥራ መለወጥ ይገባዋል፡፡
Wednesday, April 26, 2017
የትንሣኤ በዓል ትርጕሙና አከባበሩ
በሊቀ ትጉሃን ኃይለ ጊዮርጊስ ዳኘ
ሚያዝያ ፲ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሰን!
«ትንሣኤ» የሚለው ቃል የግእዝ ቃል
መገኛው ‹ተንሥአ = ተነሣ› የሚለው ግስ
ሲኾን፣ ትርጕሙም መነሣት፣ አነሣሥ፣ አዲስ
ሕይወትን ማግኘት ማለት ነው፡፡ ‹ትንሣኤ› በየመልኩ፣ በየዓይነቱ ሲተረጐም አምስት ክፍል አለው፤
የመጀመርያው ትንሣኤ ሕሊና
ነው፤ ይህም
ማለት ተዘክሮተ እግዚአብሔር (እግዚአብሔርን ማሰብ)
ነው፡፡
ሁለተኛውም ትንሣኤ ልቡና
ነው፤ የዚህም ምሥጢሩ ቃለ እግዘብሔርን መስማትና በንስሐ እየታደሱ በሕይወት መኖር
ነው፡፡
ሦስተኛው ትንሣኤ ለጊዜው (በተአምራት) የሙታን በሥጋ
መነሣት ነው፡፡ ነገር ግን በድጋሜ ሌላ ሞት ይከተለዋል፡፡
አራተኛው ትንሣኤ ክርስቶስ በሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጎ መነሣቱን ያመላክታል፡፡
የርእሰ ትምህርታችን መነሻም ይህ ነው፡፡
አምስተኛውና የመጨረሻው የትንሣኤ ደረጃ የባሕርይ አምላክ የጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ መሠረት ያደረገ ትንሣኤ ዘጉባኤ ሲኾን፣ ይህም ከዓለም ኅልፈት በኋላ
ሰው ዅሉ
እንደየሥራው ለክብርና ለውርደት፣ ለጽድቅና ለኵነኔ በአንድነት የሚነሣው የዘለዓለም ትንሣኤ ነው፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)