Saturday, September 9, 2017

መልካም አዲስ ዓመት !


እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም አሸጋገረን!
አዲስ ዓመት ሲመጣ መልካም ምኞትንና ብሩህ ተስፋን ሰንቆ ነው፡፡ በአዲስ ዓመት ዓመቱ የዕድገት፣ የብልፅግና፣ የሰላም ዘመን ይሁንልን የምንባባለው ከዚህ መልካም ምኞትና ብሩህ ተስፋ የመነጨ ነው፡፡
አዲስ ዓመትን ቤት እንዳፈራ ዶሮ፣ በግ፣ … አርዶ በዓሉን ማክበር ብቻ ሳይሆን ሰው ራሱ ከዘመኑ ጋር አብሮ በአስተሳሰብ መታደስ በሥራ መለወጥ ይገባዋል፡፡

አንዳንዶች ራሳቸው አርጅተው ሳሉ በየዓመቱ አዲስ ዓመትን ያከብራሉ፡፡ እዚህ ላይ እርጅና የእድሜ መጨመር አለመሆኑን ልብ ይለዋል፡፡ እሱማ የተፈጥሮ ፀጋ፣ ሁሉ የማያገኘው የዘመን ፍሬ፣ የእድሜ ጣርያ ነው፡፡
ተዲያ እርጅና ምንድን ነው ትለኝ እንደሆነ፡ ሰው በሐሳቡ ያረጃል፣  ሰው በቃሉ ያረጃል፣ ሰው በሥራው ያረጃል፡፡ ይህም ሐሳቡ ክፉ፣ ቃሉ የትዕቢት፣ ተግባሩ እኩይ ሲሆን ነው፡፡ እኒህ ለሰነፍ ገንዘቡ ናቸው፡፡
ሰው አዲስ ዓመትን ሲያከብር ከልቡ ተንኮልን፣ ክፋትን፣ ዘረኝነትን፣ ምቀኝነት፣ ጎጠኝነትን፤ ከሐሳቡ ትዕቢትን፤ ከሥራው በደልን፣ ፍርድ መጓደልን አስወግዶ በመታደስ በአዲስ ዓመት ወልዶ ለመሳም፣ ዘርቶ ለመቃም፣ ሠርቶ ለማደግ መዘጋጀት ያስፈልገዋል፡፡
እንግዲህ አሮጌው ዘመን አልፎ ወደ አዲሱ ዘመን ስንሸጋገር ያረጀ ማንነታችንን ትተን አዲስ ሰው በመሆን ለአዲስ ስኬት በአዲስ አስተሳሰብ፣ በመልካም እቅድ በአዲስ መንፈስ፣ እንደ ታታሪዋ ንብ በፍቅር በአንድነት ለሥራ እንነሳ፡፡
ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱእንዲል ኤፌ. 424





አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር የመልካም ሥራ ስኬት ዘመን ይሁንልን፡፡





No comments:

Post a Comment