እንደምን ዋላችሁ ውድ የማኅቶት
እድምተኞች! በማኅቶት ኪነ ጥብብ ገጽ ላይ በአበው ብሂል እንጨዋወት
የተሰኘ አበቶቻችን ደስታን፣ ሀዘንን፣ ፍቅርን፣ ቁጭትን፣ … ወዘተ የሚገልጹበት ሀይማኖታዊ፣ ባህላዊ፣ ታሪካዊ፣ማሕበራዊ ጉዳዮችን
የሚዳስስ
የአበው ጥልቅ ቅኔያዊ ንግግር መመርያና መመርመርያ ጨዋታ
ተጀምሯል፡፡ ሁላችሁም ጥያቄዎችን በመመለስ፣ ቅኔዎችን አሰባስባችሁ በመላክ፣ እንዲሁም በምትችሉት ሁሉ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡
ጥበበ አበው እንዳይዘነጋ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ ነው፡፡ እኔ ሃሳቡን ካቀረብኩ እናንተ እንደምታስፋፉት እምነቴ ነው፡፡ ለሁሉም
እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ አሜን!
እስቲ ለዛሬ መነሻ እንድትሆነን
ይህችን ቅኔ ሞክሩአት፡፡
አፈር መልሱ እንጂ ድንጋይ ለምናችሁ፣
የቀለም ቀንድ ነው ትሰብሩታላችሁ፡፡
ጥያቄ፡ ሀ. ሕብረ ቃሉ ...........................................................
ነው፡፡
ለ. ሰሙ …………………………………………………………………. ነው፡፡
ሐ. ወርቁ ………………………………………………………………. ነው፡፡
No comments:
Post a Comment