Saturday, January 30, 2016

ለዓይን ቆጣሪ ቢኖር

እንደምታዩት እኔ ዐይነ ስውር ነኝ። ቀላል አይደለም እንኳን ዘውትር ዓይን አጥቶ አንድ ቀን መብራት ሲሄድ ስንት እንደምታማርሩ ታውቅታላችሁ። አንድ ቀን ግን አልቅሼ አላውቅም።
ከሞት ወዲያ መብራት አለ። ከመቃብር በላይ መብራት አለ። ወደ መቃብር ሲወርድ ማንም ሰው ዓይነ ስውር ነው። ማንም ዐይኑ እያየ የተቀበረ የለም። ተስፋችን ግን ምንድን ነው? ከሞት ወዲያ ሕይወት አለ። ከሞት ወዲያ ብርሃን አለ። አንድ አንድ ጊዜ እመኛለሁ። የማይረባ ነገር ስናይ ዓይናችንን የሚያጠፋ ቆጣሪ ቢኖር፡፡ መልካም ነገር እስክናይ ድረስ ለጊዜው የሚያጠፋ ቆጣሪ ቢኖር። አሁን እንደው ጆሮ በካርድ የሚሰራ ቢሆን ሐሜት እንሰማ ነበር? የምንፈልገውን ብቻ አውርተን ስዊች ኦፍ እናደርገው ነበር። ስንት ዞማ ጸጉር ይዞ አስተሳሰቡ የከረደደ አለ። ጀርመን ሀገር ሄጄ ሲነግሩኝ፤ ባለ አምስት ኮከብ የውሻ ሆቴል አለ ተባለ። እኛ ሀገር አምስት ኮከብ ሆቴል ገብተው የበሉ ትንሽ ዝና ሀብት እና ትንሽ ሥልጣን ያላቸው ናቸው። ማን ይገባል ከነሱ ውጪ። ግን ሰዋች ነን። የጀርመን ውሻ ዛሬም ውሻ ነው፡፡ ለዘላለምም ውሻ ነው። እኛ ግን ሰው ነን። እንደ ሰው አስቡ ምዕመናን በማርያም። የንጉሠ ነገሥቱ የክርስቶስ አልጋ ወራሾች ነን፡፡ የደስታችሁ ልኬት የደስታችሁ ሚዛን ምግብና መጠጥ አይሁን፤ መኪናና ቤትዝናንም አታርጉ። እኛ መለኪያችን ጽድቅ ነው። መከኪያችን መንግሥተ ሰማያት ናት። ያ የምንገባበት ቤት ደግም የተዋበ፣ የደመቀ፣ መብራት ውሀ የማይሄድበት፤ ሃያ አራት ሰዓት ክርስቶስ የሚያበራበት፤ ሃያ አራት ሰዓት የሕይወት ውሀ የሚጠጣበት፤ ሀብታም፤ ደሀ፣ ተራ ሰው የማይባልበት፣ እገሌ ግባ እገሌ ውጣ የማይባልበት ቦታ ነው።

(ከሊቃውንት አንደበት የተወሰደ)






No comments:

Post a Comment