ሆነን እንኖራለን፣ እንዘልቃለን ብዬ
ጋቢ፣ ቡሉኮዬን፣
ቁምጣ መጫማዬን
ስለግሰው ኖሬ
እጅ አጠረኝና ስሄድ በባዶ እግሬ
ብሶበት አየሁት፡፡
በሉ ብሶብኛል፣ እኔም እርቃኔን ነኝ በሉና ንገሩት
እንዲያ ተቸግሮ ሲሄድ እንዳየሁት
እኔንም እንዲያየኝ
አይቶም እንዲያዝንልኝ
በዘመናት ችግር በእንባ ጎርፍ ሞጭሙጮ ለታወረው ዐይኑ ዐይኔን መጽውቱልኝ፡፡
በአከል ንጉሴ ፍላሎት 2006 ዓ/ም
ምንጭ፡- ሪፖርተር ገዜጣ ታሕሳስ
20 ቀን 2008 ዓ/ም ረቡዕ እትም ገጽ 25
No comments:
Post a Comment