Friday, September 11, 2015

እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሓንስ በሰላም በጤና አሸጋገራችሁ ፡፡

ትናንት ከእኛ ጋር የነበሩ ዛሬ አብረውን የሌሉ ዓረፍተ ዘመን የገታቸው አብረውን ከዘመን ዘመን ያልተሸጋገሩ  እንኳን አደረሳችሁ የማንላቸው ፣ የማይሉን ብዙዎች ናቸው ፡፡ ይህ ሁሉ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ፡፡ የዓለምን ዕድሜ የወሰነ የእኛን ዘመን የቀመረ ፣ ያለፉትን በዓረፍተ ዘመናት የገታቸው ፣ እኛን በሕይወተ ሥጋ ጠብቆ የንሥሓ ገዜ የጨመረልን የዘመናት ጌታ እርሱ እግዚአብሔር ነው ፡፡

Wednesday, September 9, 2015

ወርኃ ጳጉሜ

እንኳን ለወርኃ ጳጉሜ በሰላም አደረሰን
የዘመናት ጌታ ቸሩ አምላካችን ቀሪውን ተረፈ ዘመን በሰላም አስፈጽሞ ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሓንስ ያሸጋግረን ፡፡ አሜን ፡፡
ውድ የማኅቶት ዘተዋሕዶ እድምተኞች እንደምን ከረማችሁ ?
ከዚህ በመቀጠል ውሉደ ተዋሕዶ ለፌስ ቡክ ገጼ ላይ ጳጉሜ ምን ማለት ነው ? ለምንስ አምስትና ስድስት ቀን ሆነች ? ብለው ለጠየቁኝ ጥያቄ አጠር ያለች መልስ እሰጣለሁ ተከታተሉኝ ፡፡ መልካም ንባብ ፡፡